እነ ለማ መገርሳ ፍርድ ቤት ቀርበው ነገ ሊመሰክሩ እንደሚችሉ ተገለፀ

0
2195

በጌታቸው ሺፈራው (ፌስ ቡክ ገፅ)

27-12-2017

በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከሳሾች በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ ለማ መገርሳ፣ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ወ/ሮ ጫልቱ ሰኒ እና አቶ አባዱላ ገመዳ ነገ ታህሳስ 19/2010 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው ሊመሰክሩ እንደሚችሉ መግለፃቸው ታውቋል።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉት ተከሳሾች ጠበቃ አቶ አብዱልጀባር ሁሴን ባለስልጣናቱን በአካል አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ዛሬ ታህሳስ 18/2010 ዓም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ በሁለቱ ቀን ቀጠሮ በስብሰባ ምክንያት መቅረብ እንዳልቻሉ፣ ለነገ ታህሳስ 19/2010 ዓም ቀርበው ሊመሰክሩ እንደሚችሉ ገልፀውልኛል ሲሉም ጠበቃው ለችሎቱ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል የ4ኛ ተከሳሽ በቀለ ገርባ የመከላከያ ምስክር የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ዛሬም ያልቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥብቅ ትዛዝ እንዲሰጥ ጠበቃ አብዱልጀባር ጠይቀዋል።