እውነተኛ እርቅ የሚመጣው እንዴት ነው? – ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ፣ ጠበቃ ሞላ ዘገየና መምህር መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ ይናገራሉ

0
1854

በጀርመን ድምጽ ራድዮ “በኢትዮጵያ የፖለቲካ መቻቻል እንዴት?: በሚል ርዕስ የተወያዩልት፤ ፕሮፊሰር ብርሃኑ መንግስቱ በዩናይትድ ስቴስትስ ኦልድ ዶሚኒየን ዮንቨርስቲ መምህርና የግጭትና መንስኤ ላይ የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ ግጭት አፈታትና እርቅ ላይ ስልጠናን በመስጠት ላይ የሚገኙ፤ የዉይይት መጽሔት ዋና አርታዒ ጠበቃ ሞላ ዘገየ፤ እንዲሁም በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉት፤ በሰዋሰዉ ብርኃን ቅዱስ ጳዉሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአዲስ ኪዳን መምህር መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ ናቸዉ። አወያይዋ የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛ አዜብ ታደሰ ናት::