“አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ” ማን ነው?

0
1717

ባሕር ዳር፡ ታህሳስ 04 / 2009 ዓ.ም (አብመድ)
✍በየሺሀሳብ አበራ

Image may contain: 1 person, beard
ከአቀበቱ ማዶ አንዲት ውብ የገጠር ልጅ ከብቶቿን ወደ ተራራ
ታወጣለች ፡፡ህፃኗ የፀጉር አሰራሯ፣ተፈጥሮ ሳትነፍግ የለገሰቻት
ውበት መግነጢሳዊ ሀይል ፈጥሮ ይስባል፡፡
እኔም ተስቢያለሁ፡፡ ህፃኗ ከመልከ ቀናነቷ ባለፈ ድምፀ መረዋ ናት፡፡ ከብቶቿን
” አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ” በሚል ዘፈን ታዝናናቸዋለች፡፡ነገሩ
ራሷን ነው የምታዝናና፡፡ እኔም ድምጷን ካደነቅሁ በኃላ አያሌው
አባትሽ ናቸው ??ከሆኑስ አቶ አያሌው ለምን ሞኝ ሆኑ ብለሽ
ትዘፍኛለሽ አልኳት?
እንደመጣልኝ ለአንደበት መክፈቻ ብቻ፡፡
ሚጡ መለሰች”፣አያሌውማ ድሮ ድሮ የነበረ ሰው ነው፡፡ እና እሱም ሲበዛ ሞኝ ነበር፡፡ ሞኝ የሆነው ደግሞ ሞኝ ሁኖ ተፈጥሮ ሳይሆን ሰው አምኖ ነው፡፡”አለችኝ አንገቷን ቀብራ፡፡ ስለ አያሌው ሞኙ ህፃኗ ከእኔ በላይ መናገር መቻሏ አስገረመኝ፡፡ አለማወቄን ሰደብኩት፡፡
ከዘፈኑ ውጭ አያሌው ሞኙ ተረት ይሁን ገፀባህሪ ፣ንጉስ ይሁን
ባለሟል አላውቀውም ፡፡
ለህፃኗ ምላሽ እንዴት ሳልል ትክክለኛ አያሌው ምኙን ፍለጋ ከመፅሀፍት ከምን ፈለግሁ ፡፡
እነሆ የፍለጋየ በረከት!!!!!
❖❖❖
አያሌው ሞኙ ፊታውራሪ አያሌው ብሩ ናቸው፡፡ፊታውራሪ አያሌው
ብሩ የራስ ብሩ ወልደሚካኤል ልጅ እና የእትጌ ጣይቱ የቅርብ
ዘመድ ናቸው፡፡ ፊታውራሪ አያሌው የወገራ አውራጃ
ሹመኛ፣ የጎንደር አስተዳዳሪ እና በአፄ ሀይለስላሴ ዘመን የንጉሰ
ነገስቱ ጦር አዛዥ ነበሩ፡፡ ፊታውራሪ በመኢሶ ጦርነት ልጅ እያሱ
እንዲወድቅ ፣በአንቺም ጦርነት ራስ ጉግሳ ስልጣን እንዲለቅ
በማድረግ አፄ ሀይለስላሴ ስልጣን እንዲይዙ አድርገዋል፡፡
❖❖❖
አፄው ለዚህ ሁሉ ውለታው የራስነት ማዕረግ እንደሚሰጧቸው
ለአያሌው ሞኙ ቃል ገብተውላቸው ነበር፡፡
❖❖❖
ዳሩ ግን አፄ ሀይለስላሴ የስልጣን መንበራቸውን ካስተካከሉ
በኋላ አያሌው ብሩን ፊት ነሷቸው፡፡ምክንያቱም፣ ፊታውራሪ
አያሌው ፣የእትጌ ጣይቱ የቅርብ ዘመድና የአፄ ሚኒሊክ
ባለስልጣናት የቅርብ ወዳጅ ስለነበሩ ወንበሬን ሊጋፋ፣አመፅም
ሊያስነሳብኝ ይችላል በማለት ለፊታውራሪ አያሌው የተሻለ
ማዕረግ ሳይሰጧቸው ቀሩ፡፡
እንዳውም ከንጉሡ የክብር ፕሮቶኮልነት ሁሉ አውርደው በቅጣት ወደ አርሲ ላኳቸው፡፡
አያሌውም የገዛ ዘመዶቻቸውን ተዋግተው ስልጣን አሳልፈው
ለአፄ ሀይለ ስላሴ መስጠታቸውን እንደ ረመጨት ፈጃቸው፡፡
አቃጠላቸው፡፡ይሄን የተመለከቱ ደግሞ ” አያሌው ሞኙ ሰው
አማኙ “አያሌው ሞኙ ንጉስ አማኙ” እያሉ ዘፈኑባቸው፡፡ ዘፈኑም ባህል
ሁኖ እስከዛሬ ድረስ በጎንደር ፣በጎጃም፣በወሎ በስፋት
ይዜማል፡፡
በምንጭነት፡-
– Ethiopian patriot in 20th century
– ከዲያቆን ዳንኤልን ክብረት በአያሌው ብሩ ህይወት ዙሪያ
የተፃፈውን “የተደበቀው ማስታወሻ” የሚለውን መፅሃፍ ዋቢ
አድርጎ ከፃፈው ተጠቅሜያለሁ፡፡

ምንጭ: የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት