Re: Ethiopian Prisons and Prisoners of Consistence- an Insider’s Diary

0
549

ታህሳስ 2003 ዓም

ጉዳዩ – በወያኔ እስር ቤቶች ሞልቶ ስለፈሰሰው የወገኖቻችሁ ስቃይና ሰቆቃ እንድታውቁት

1. ትንሽ ስለ ራሴ

በወያኔ የወንጀል ምርመራ፣ የወህኒና የእስር ቤቶች አስተዳደር አካባቢ የምሰራ የፖሊስ፣ የፌደራልና የደህንነት ባልደረባ ነኝ። ባጭሩ እንድታውቁት የምፈልገው በሃገሪቱ እስር ቤቶችና ማእከላዊ እየተባለ

በሚጠራው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን እስር ቤት ጨምሮ ስለሚካሄደው የእስረኞችና የአሳሪዎች ግንኙነት፣ ስለእስረኞች አያያዝ፣ በእስረኞች ላይ ስለሚፈጸም ግፍና ሰቆቃ ማወቅ የምችልበት የተወሰነ እድል ያለኝ ሰው መሆኔን ነው። የሃገሪቱ እስር ቤቶች ስል በይፋ ስለሚታወቁት

ዋና ዋና የፌደራል መንግስቱ እስር ቤቶች ማለቴ እንጅ በወያኔ የደህንነት ሃላፊዎች በአዲስ አበባና በየክልሉ በድብቅ ሰለተመሰረቱት እስር ቤቶች ማለቴ አይደለም። ወይም በየክልሉ በየዞኑና በየወረዳው በክልል ንጉሶች ስር ስለሚተዳደሩት በሽዎች የሚቆጠሩ ማጎሪያ ጣቢያዎች አይደለም። ዛሬ

በኢትዮጵያ ውስጥ የእስረኛው ብዛት ደርግ ከፍተኛ ግፍ ሲፈጽምበት ከነበረበት ከ1969 እስከ 1970 ከቆየው ዋናው የቀይ ሸብር ዘመን ጋር ሲነጻጸር በትንሹ ከ50 እጥፍ በላይ አድጓል። ይህ እየሆነ ያለው እንደደርግ ዘመን ወያኔን በከተማና በገጠር የሚፋለሙ ጠንካራ ተቃዋሚዎች በሌሉበት ሁኔታ መሆኑ

ደግሞ ሁላችንንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ ነው። በመላው ሃገሪቱ ሰለተበተነ ህጋዊና (በወያኔ ህግ ማለቴ ነው) በህገወጥ መንገድ ስለታሰረ በብዙ አስር ሽዎች ስለሚቆጠር እስረኛ ልወቅ ብልም የማውቅበት አቅም የለኝም። ከዚህ በታች የማቀርብላችሁ መረጃ የተሰባሰበው ራሴ ባይኔ ካየሁት፤በጆሮዬ ከሰማሁት፤ ለዚህ ስራ ሊተባበሩኝ ቃል ከገቡ ጥቂት ባለደረቦቼና በጣም አነስተኛ ወጪ

በሚጠይቅ የመጠጥና የምግብ ግብዣ እንደዋዛ በየአካባቢያቸው የሚያዩትን ጉድና ጉዳይ እኔን ለማጋራት ፈቃደኛ ከሆኑ የፖሊስና የደህንነት አባላት ነው።

2. የሪፖርቱ አላማ

እኔም ይህን ሪፖርት ለእናንተ ለወገኖቼ ስልክላችሁ አንድ ሰሞን ጉድ ብላችሁ እንድትረሱት አይደለም። እኔ በሬን ዘግቼ ጨለማን ተገን አድርጌ አልቅሻለሁ። እናንተም እንደኔ አልቅሱ።ባደባባይ ይሁን በድብቅ የማልቀሱን ምርጫ ለእናንተ ትቼዋለሁ። ዋይ ወገኔ! ዋይ ሃገሬ! ብላችሁ ግን አምራችሁ አልቅሱ ። ለሃገራችሁ ፣ለህዝቧና በተለይ በወያኔ አሳሪዎች እጅ የወደቁት የሃገራችሁ ልጆች ስቃይ ተሰምቷችሁ እንድታለቅሱ እፈልጋለሁ። አልቅሳችሁ ግን ዝም እንድትሉ አይደለም። በተለይ በውጭ ሃገር የምትገኙ ኢትዮጰያውያን በዚህ ሃገር እስር ቤቶች ውስጥ የሚፈጸመውን በዘር የተደራጀና

በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ በግለሰቦች ላይ የሚዘንበውን ሰቆቃ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የአለም የቀይ መስቀል ድርጅት፣ የሁማን ራይትስ ወች፣ የአምነስቲ ኢንተርናሺናል፣የጄኖሳይድ ወች ድርጅት፣ በሄግ የሚገኘው የአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት፣ የአሜሪካን ስቴት

ዲፓርትመንት፣ የአውሮፓ ፓርላማ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሌሎችም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ግፎችን የሚዘግቡ፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ የሚታገሉ ሁሉ እንዲያውቁት እንድታደርጉ ነው። “ምን ዋጋ አለው?” ትሉኝ ይሆናል። አዎን ዛሬ ምንም ዋጋ ላይኖረው ይችላል። ብዙዎቹ መንግስታትና

ድርጅቶች የወያኔን ግፈኛነትና ጨካኝነት ያውቃሉ። በተለይ የምእራብ መንግስታት ይህን እያወቁ ነው አይቶ እንዳላየ የሚሆኑት። እኔን ጨምሮ በርካታዎቹን ያሰለጠኑን ለስልጠናችንም የሚሆነውን ወጪ

የሸፈኑት እንግሊዞች ናቸው። በዚህም ውለታቸውና ወያኔም ኢትዮጰያዊ ለሆነ ነገር ሁሉ ባለው ጥላቻ

2

የተነሳ የማእረግ ስማችን ሳይቀር እንደዱሮው አስር አለቃ፣ ሃምሳ አለቃ፣ የመቶ አለቃ፣ ሻምበል ወዘተ መሆኑ ቀርቶ የእንግሊዞችን የማእረግ ስሞች እንድንወርስ ተደርገናል። እኛም ሆንን ህዝባችን የማያውቀውን በቅጡ እንኳን ልንጠራው የማንችለው፤ ለተራ ፖሊስ- ኮንስታብል፣ ለባለማእረጎቹ

ምክትል ሳጅን፣ ሳጅን,፣ ሱፐር ኢንቴንዳንት፣ ምክትል ኢንስፔክተር፣ ኢንስፔክተር፣ ምክትል ኮሚሽነር ኮሚሽነር ወዘተ የሚሉ የእንግሊዝ ስሞች የተለጠፈልን እንግሊዞች መኪና፣ ዱላ፣ ልብስ እና ስልጠና

ስለሰጡን ነው። ዛሬ በየእስር ቤቱ ሰው የሚገርፉት፣ በየመንገዱ ህጻናትን የሚገድሉት እነ ሃምሳ አለቃ አይደሉም ።እነ ኮንስታብል እገሌ እነ ሳጅን እገሌ፣ እነ ሱፐር ኢንቴንዳንት እገሌ ናቸው። ትእዛዝ ሰጪዎቹ እነ ምክትልና ዋና ኮሚሽነር እገሌ ናቸው። ይህንን እንግሊዞች ያውቃሉ። ይህን እያወቁ

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወያኔ ለሚፈጽመው ወንጀል ተባባሪ መሆንን መርጠዋል። ወያኔን በከፍተኛ ደረጃ በገንዘብ የሚደጉሙት፣ በዲፕሎማሲ መድረኩ እክል እንዳይገጥመው ድጋፍ የሚያደርጉለት ሆነው አርፈውታል። ከዚህ በላይ የአንድ ሃገርና ህዝብ ጠላትነት ምን ሊሆን ነው? ለማለት የፈለግሁት የምእራብ መንግስታት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ አይተው እንዳላዩ እንደሚያልፉት አውቃለሁ ለማለት ነው። ይህንን መረጃ ስልክ ዛሬውኑ አንድ ነገር ይሆናል ከሚል ቅዠት አይደለም።

ነገ የሚባል ነገር መኖሩን መርሳት የለብንም። የዛሬ የሃገራችን እብሪተኛ ገዢዎች ነገ ቀን ሲጎድልባቸው እነዚህን መረጃዎች አሰባስበው ከሳሽ ለመሆን የሚሽቀዳደሙት እነዚህ እንደወያኔ ይሉኝታ የማያውቁ የምእራብ ሃገሮች ስለሆኑም መረጃው በእጃቸው ቢገባ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም ለማለት ነው።

አቅም ያላችሁ ይህንን ዘገባ ተርጉማችሁ ለምእራብ የሚድያ ሰዎች፣ የሰው ልጅ መብት መጣስ ለሚያሳስባቸው የፓርላማ ተመራጮች የሲቪል ድርጅት መሪዎች አድርሱልኝ። በእናንተ በወገኖቼ በኩል የሚደረገው ይህ ብቻ አይደለም። ይህ ብቻም በቂ አይሆንም። ይህ ዘገባ በዋነኛነት የሚያተኩረው ከግንቦት 7 ጋር በመተባበር መፈንቅለ መንግስት ልታካሂዱ ነበር ተብለው በታሰሩት በዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ በዘራቸው በአብዛኛው አማራ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ቢሆንም በነዚህ

ግለሰቦች ላይ የደረሰው አስከፊ ሰቆቃ በሁሉም የሃገሪቱ ዜጎችና ዘሮች ላይ የሚፈጸም ነው። በግንቦት

ሰባት አባልነትም ተጠርጥረው የታሰሩት በሙሉ የአማራ ዝርያ ያላቸው ብቻ እንዳልነበሩም መታወቅ

ይኖርበታል። ከወያኔ ዘረኛነት የሚመጣ ጭካኔ ያላረፈበት ዘር በሃገሪቱ ውስጥ አይገኝም። የኦሮሞው፣

የጋምቤላው፣ የኡጋዴኑ፣ የሲዳማው፣ የጉጂው እና የሌላውም ዘር ስቃይና መከራ ምድሪቱ

ከምትሸከመው በላይ ሆኗል። ይህን ተረድታችሁ ይህንን በሁሉም የሀገሪቱ ህዝብ ላይ የሰለጠነ

የዘረኞች ጭካኔ እንዲያከትም በአንድነት ተባብራችሁ እንድትነሱ ነው። ሌላው ፍላጎቴ ዜጎች ይህን መንግስት እንደ አንድ ጤነኛ መንግስት በመውሰድ ከዚህ መንግስት ጋር እስካሁን የገቡበትን ማናቸውንም ግንኙነት በቅጡ እንዲፈትሹ ነው። በኔ እምነት ከዚህ መንግስት ባለስልጣናት ጋር  የሚወዳጁ፤ ከዚህ መንግስት ጋር ተሻርከው የሚነግዱ፤ በዚህ መንግስት ግብዣዎች ላይ የሚገኙ፤ ይህ መንግስት የሚጠይቃቸውን የሚፈጽሙ የሃገሪቱ ዜጎች ከምን አይነት ጨካኝ አረመኔ ሰዎችና መንግስት ጋር እየሰሩ እንደሆነ እንዲያውቁት ነው። የወያኔ መንግስት እጅግ አስከፊ የሆነ ግፍና ወንጀል በበርካታ የሃገሪቱ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ነው። ከዚህ ወንጀለኛ መንግስትና ባለስልጣናት ጋር ስራችንና ኑሯችን ከሚያስገድደን በላይ መወዳጀት እራሱ ወንጀለኛ ሊያደርገን እንደሚችል ማወቅ ይኖርብናል።

 

3. ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች

ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ዘገባ ግፉን በሚፈጽሙት የታችኛዎቹ አካላት ፍላጎትና እውቅና ብቻ የሚፈጸም አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአቶ መለስ ዜናዊ አንስቶ ከሳቸው በታች በሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የደህንነት ሹሞች እንዲሁም ከፍተኛ ዳኞች እያወቁት የተፈጸመና እየተፈጸመ ያለ ጉዳይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌቪዝንና በሬድዮ ቀርበው “በግንቦት ሰባት ስም የታሰሩት 3 እስረኞች ድብደባ ደርሶብናል የሚሉት ሃሰት ነው” ብለው ሲናገሩ ከዱላም በላይ ያለፈ ስቃይ በቀጥታ ራሳቸው በሚሰጡት ትእዛዝ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ጠንቅቀው እያወቁ ነበር። ሌሎችም ባለስልጣናት አልሰማንም አላወቅንም እንዳይሉ በዚህ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን መረጃዎች በግል እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በተለይ ወያኔን አቅፈውና ደግፈው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ዘረኛ የግፍ ስርአቱን እንዲዘረጋ ለረዱት የብአዴን አመራሮች እንዲደርሳቸው ተደርጓል። የሚያሳዝነው በዘገባው ውስጥ አንዳንዶቹ ታሳሪዎች በትግራይ ገራፊዎቻቸው ሲቀጠቀጡ የነበረው “የትኛው የብአዴን አመራር ነው አይዞህ ያላችሁ?” እየተባሉ፣ እነዚሁኑ ለራሳቸው ክብር የሌላቸውን አመራሮች ሳይቀር

እንዲወነጅሉ ለማድረግ ጭምር እንደነበር የብአዴን አመራሮች መረጃው ደርሷቸዋል። እነዚህ የአማራንና የተቀረውንም የኢትዮጵያ ህዝብ እጅ እግሩን አስረው በወያኔ ዘረኞቸ ተገዶ እንዲደፈር ያደረጉ ወራዶች በጉዳዩ ላይ እስከአሁን አንድም ቃል አልተነፈሱም፤ ወደፊትም ይተነፍሳሉ የሚል እምነት የለኝም። የአማራን ህዝብ እወክላለሁ የሚል ድርጅት የገዛ ድርጅቱ አባላት በሽዎች ከስራቸው ሲባረሩ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት እጅግ አሰቃቂ በሆነ እስር እጅግ አሰቃቂ የሆነ ቅጥቀጣ ሲፈጸምባቸው፣ የአማራ ተወላጆች በመሆናቸው ዘራቸው እየተጠራ እጅግ አሰከፊ በዘር ላይ የተመሰረተ ስድብና ውርደት ሲደርስባቸው የወያኔ ዘረኛ ገራፊዎችና ተሳዳቢዎች አጨብጫቢና አጫፋሪ መሆናቸው ወደፊት በታሪክ ፊት ውድ ዋጋ የሚያስከፍላቸው ለመሆኑ ጥርጣሬ የለኝም።

 

4. ወንጀል ተብሎ ስነቀረበው ነገር

የዛሬው ሪፖርት የሚያተኩረው ወያኔ ከነጄነራል ተፈራ ማሞ ጋር ባሰራቸው ግለሰቦች ላይ በተለይ በተለምዶ ማእከላዊ ምርመራ በተባለው የምድር ሲኦል ውስጥ በደረሰባቸው እጅግ ዘግናኝ ሰቆቃ ላይ ነው። እግረ መንገዴን ግን ይህ እስር ቤት ምን እንደሚመስል በስር ቤቱ ውስጥ በሌሎች ላይም ስለሚደርሰው ሰቆቃ ጥቂት ማለቴ አልቀረም። እድሜ ከሰጠኝ፤ የምሰራውን ከሚያውቁ ጓደኞቼ መሃል ለጥቅም ሲሉ ከድተው ካልያስያዙኝ ወይም ወያኔ በጥርጣሬ ካልደረሰብኝ ወደፊት እንድታውቁት የማደርገው ብዙ የወያኔ ገበና ይኖረኛል። አደገኛ ስራ ነው ትሉኝ ይሆናል፤ አውቃለሁ። ከውርደት ህይወት ሞት ይሻላል ብዬ ሰለማምን የመጣውን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። እናንተም ወገኖቼ የኔን ድካምና መስዋእትነት መና እንደማታስቀሩት ተስፋ አለኝ። የግንቦት 7 ተከሳሾችን ለመያዝ ዝግጅት የተጀመረው አብዛኛው ታሳሪዎቹ ከታሰሩበት ከሚያዚያ 16 2001 አመተ ምህረት ሁለት ቀናት

በፊት ቀደም ብሎ ነበር። ለስርአቱ ያላቸው ታማኝነት በትግራይ ተወላጅነታቸው የሚለካው ጥቂቶች  የምርጡ ዘር አባል የሆኑት የስራ ባልደረቦቻችን ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ ተነግሯቸው ነበር።

የትግራይ ደም የሌለን ሰራተኞች ግን የምናውቀው ነገር አልነበረም። ይሁንና ሚያዚያ 14 እና 15 ቀን 2001 አመተ ምህረት “የመረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ የጸረ ሽብር ሃይል” በሚል የሚታወቀው በትግራይ ተወላጆች የተሞላው ቡድን በማእከላዊ ምርመራ ውስጥ በሚያደርገው ያልተቋረጠ ስብሰባ፣ አባላቱ በሚያሳዩት ያልተለመደ ጥድፊያ የተሞላበት እንቅስቃሴ፣ መንሾካሾክና ሽር ጉድ እንዲሁም ያለማቋረጥ በሚደወለው ስልክ ብዛት ይህ ቡድን እኛ የትግራይ ተወላጆች ያልሆንነው ሁለተኛ ዜጎች እንዳንሰማው የተፈለገ ትልቅ ጉዳይ እንደያዘ ለመጠርጠር አልተቸገርንም።

የጠረጠርነው አልቀረም። እነዚህ ምርጥ ዘሮች በር ዘግተው ማንም የትግራይ ተወላጅ ያልሆነን ሰው ሳያማክሩ ያዘጋጁትን የአፈና እቅድ አጠናቀው ከደህንነት፣ ከፌደራልና ከመደበኛ ፖሊስ አካላት ታማኝ ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን የራሳቸውንና ከሌላ ዘር የተቀላቀሉ ተራ ወታደሮችና ባለሌላ ማእረጎች በማሳተፍ የግንቦት 7 ተከሳሾችን መያዝ የጀመሩት ሚያዚያ 16 2001 አመተ ምህረት ከሰአት በኋላ ነበር። በዚህ የማሰር ስራ የተሰማሩት የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ አባላት በሙሉ የተነገራቸው ግዳጅ እንደሚወጡ እንጂ ግዳጁ ምን እንደነበር አልነበረም። ተራው የትግራይ ፖሊስ ሳይቀር ግን ግዳጁ ምን

እንደነበር በደህንነቱና በፌደራል ፖሊሱ ወስጥ ወያኔ በዘረጋው የትግራይ ተወላጆች ዘረኛ መዋቅር 4 አማካይነት ዘረኛ ከሆነ መርዝ ጋር ተቀላቅሎ እንዲያውቀው ተደርጎ ነበር። እኛንም ከሌላ ዘር የመጣን የደህንነትና የፌደራል ፖሊስ አባላትንም በአይነ ቁራኛ መጠበቅ ለወያኔዎቹ ከተሰጣቸው የስራ መደብ ጋር የተያያዘ እንደነበር አናጣውም፤ የተለመደ አሰራር ነውና። ይህ ግዳጅ በወያኔ ዘረኛነት የተንገፈገፉ፣ በተለይ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ ካለው ቂምና ጥላቻ በመነሳት የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር ለማዋረድና በፖለቲካና በኢኮኖሚ ለማድቀቅና አስጎንብሶ ለመግዛት የሚፈጽመውን አስገድዶ ከመድፈር ልዩነት የሌለውን እኩይ ድርጊት በየቦታው ሲቃወሙ የነበሩ፤ የዚህ ተቃውሞ ሬኮርድ ያላቸውን የአማራ ልጆችን ከያሉበት መልቀም መሆኑን የተረዳነው ቅዳሜ ሚያዚያ 17 ቀን የመረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ የጸረ ሽብር ሃይል ለመንግስት ሚድያዎች ያሰራጨውን ዜና እኛም በግዳጁ የተሰማራነው ሳንቀር እንደማንኛውም ህዝብ

በሬዲዮና በቴሌቪዝን ስናዳምጥ ነው። በኔ እምነትና ተሰበሰበ ከተባለው መረጃ እንዳየሁት ከየቦታው እየተለቀሙ የታሰሩት ሰዎች እጅግ አብዛኛዎቹ ወያኔ በሃገሪቱ ወስጥ እየገነባ የመጣውን በትግሬነት ላይ የተመሰረተ ዘረኛ ስርአት የሚቃወሙ የነበሩ ናቸው። አንዳንዶቹ እንደ ጀነራል ተፈራ ማሞ ያሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ባሉባቸው የብአዴን ስብሰባዎች ላይ ይህን አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ

የተቀዱት ቪድዮ በማእከላዊ ምርመራ ጽ/ቤት ይገኛል። አንዳንዳዶቹ ታሳሪዎቹም ራሳቸው በፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ቃላቸው በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል በሃገሪቱና በህዝቡ ህይወት ውስጥ ወያኔዎች ዘረኛ በሆነ መንገድ እየገነቡት ስላለው ፍጹማዊ ዘረኛ የበላይነት ለራሱ ለብአዴን አመራር ሳይቀር እንደነገሩና እንዳስጠነቀቁ ተናግረዋል። ይህን በፍርድ ቤቱ መድረክ በጆሮዬ ከሰማሁ በኋላ ሰዎቹ በተለይ የጦር መኮንኖቹ እንዲታሰሩ ግፊቱን ሲያደርጉ ከነበሩት መሃል ዋንኛዎቹ ራሳቸው ስጋቸውን ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸውን ለወያኔ የሸጡ የብአዴን አመራሮች ናቸው የሚል ወሬ በማእከላዊ ምርመራ በስፋት መወራቱ የሚያስገርም ሆኖ አላገኘሁትም። ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ነበራቸው

የሚለውን ክስ ለማመን የተቸገርነውም ለዚህ ነው። ግንቦት 7 ህብረ_ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ ሳለ በግንቦት 7 ነት ተከሰው የተያዙት ሰዎች በሙሉ ከዶክተር ብርሃኑ ዘመድ በስተቀር አማሮች ሆነው መገኘታቸው ግንቦት 7ን ሽብርተኛ ብሎ ለማወጅ ከመፈለግ ሌላ ከታሳሪዎቹ ጋር የሚያገናኘው ነገር ያለ አልመሰለኝም። ወያኔ በራሱ በብአዴን ሰዎችና በራሱ የስለላ ድርጅት የወያኔን ዘረኛ የበላይነት ይቃወማሉ፤ የአማራ ህዝብንና ምሁራንን እንዲሁም በሰራዊቱ በፌደራልና በመደበኛ ፖሊሱ ውስጥ የሚገኙትን አማሮችን ይቀሰቅሳሉ የሚላቸውን ሰዎች ለይቶ እንዳሰረ ነው የምረዳው። የታሰሩት ሰዎች

ማንነት የሚያሳየውም ይኸው ነው። ይህን የመሰለ ስራ መስራት ወያኔ የለመደበት ነው። ኦነግን ሰበብ እያደረገ በወያኔ ላይ ተቃውሞ ያላቸውን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ምሁራን፣ የሰራዊትና የፖሊስ አባላት እያፈነ በየእስርቤቱ እያጎረ ለከፍተኛ ስቃይ የዳረገበት ዘዴ ነው። ወያኔ በአደባባይ ወጥቶ “እነዚህን ኦሮሞዎች ወይም አማሮች የገደልኩት ያሰርኩት ዘረኛ የበላይነቴን ስለተቃወሙ ነው” እንዲል የሚጠብቅ ካለ፣ እሱ የዋህ ነው። ሽብር ለማካሄድ ህገ መንግስት ለመናድ ቫትና ግብር ባላመክፈል ወዘተ የሚሉ ሰበቦች ያስፈልጉታል። ግንቦት ሰባት፣ ኦነግ፣ ኦብነግ የሚባሉ ድርጅቶች

ስም በየክሱ የሚነሳውም በዘር ላይ የተመሰረተ ጥቃት ለመሸፈን ነው። ሚያዝያ 16 ቀን 2001 አመተ ምህረት መጀመሪያ በመፈንቅለ መንግስት በማግስቱ ደግሞ ክሱ ተቀይሮ በሽብርተኛነት የተከሰሱት ሰዎች አፈና የተካሄደው በሁሉም የሀገሪቱ ክልል ነበር። ከጎንደር እስከ ሃረር ድረስ በሚገኘው የሃገሪቱ ክልል የወያኔን ዘረኛነት የሚቃወሙ በርካታ ግለሰቦች እንደ አውሬ እየታደኑ ተይዘዋል። በይፋ ለፍርድ ቤት የቀረቡት ከሃምሳ የማይበልጡ ግለሰቦች ቢሆኑም የወያኔ የደህንነት አባላት በሚቆጣጠሯቸው የየክልሉ የምርመራ ጣቢያዎች የታሰሩትና እጅግ አሰቃቂ ሰቆቃ የተፈጸመባቸው የሰራዊቱ የፖሊስና

የፈደራል ፖሊስ፣ የመደበኛ ፖሊስ አባላትና የሲቪሎች ቁጥር ከመቶዎች አልፎ ወደሽዎች እንደሚጠጋ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በተሰማሩ ወጣት ምሁራን በጎልማሶች፣ በአረጋውያን፣

 

5 በሴቶችና በወንዶች ላይ እመቃው ተካሄደ። ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሆን ተብሎ ከተቀነባበረው የጥቂቶች አያያዝ በስተቀር ብዙዎቹ እስረኞች ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ የተያዙና ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ቤታቸው የተበረበሩባቸው ንብረታቸው የተዘረፉባቸው ነበሩ። የወያኔን መንግስት በአመጽ ለመገልበጥ አሲረዋል ከተባሉት መሃል አንዳንዶቹ ስርአቱን ከሚያገለግሉበት ቦታ የተያዙ ናቸው። አንዳንዶቹ ማእከላዊ እንድትመጣ ትፈለጋለህ ተብለው በራሳቸው ሄደው የተያዙ ናቸው። አንዳንዶቹ አማን ብለው ከተቀመጡበት ቤታቸው የተወሰዱ ሲሆኑ፣ ከንግድ ተቋማቸው ላይም እጅግ አስደንጋጭና አሸባሪ በሆነ ሁኔታ መትረየስና ክላሽን ያነገቡ በሃያዎችና በሰላሳዎች የሚቆጠሩ የደህንነትና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከበውና አዋክበው የየያዟቸውም አሉ። ከእነዚህ እስረኞች ውጭ

በወያኔ የደህንነት አባላት እየታፈኑ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶችና የግል መኖሪያቸው የተወሰዱ እስካሁንም የት እንደደረሱ የማይታወቁ በብዙ መቶች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች አሉ። በጥርጣሬ ብቻ ከመከላከያ፣ ከፖሊስና ከፊደራል ፖሊስ ስራቸውና መንግስት ከሰጣቸው የኪራይ ቤቶች ተባረው ቤተሰባቸውንና ራሳቸውን ለረሃብና ለእንግልት የተዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እንዳሉ መረሳት የለበትም።

 

5. ማእከላዊ ምርመራ በማእከላዊ ምርመራ ሰለደረሰው ሰቆቃ የያንዳንዳቸውን ስም እየጠራሁ ከማቅረቤ በፊት “ማእከላዊ ምርመራ” ስለሚባለው ተቋም ትንሽ ማለት ያስፈልጋል። ማእከላዊ ምርመራ በተለያዩ ተከታታይ መንግስታት ዘመን፣ መንግስት በወንጀል የሚከሳቸው ሰዎች፣ በተለይ መንግስት ጉዳያቸውን

ሊያጠብቅባቸው የሚፈልጋቸውን ታሳሪዎች በጥብቅ እስርና ምርመራ እንዲሰቃዩ የሚያደርግበት ቦታ ነው። ይህ ቦታ እንደ ደርግ ግዜ ባይሆንም በንጉሱ በአጼ ሃይለስላሴም ዘመን ጥብቅ ምርመራ የሚካሄድበት፤ አልፎ አልፎ መርማሪዎች ከታሳሪዎች ማግኘት የሚፈልጉትን ማስረጃ ለማሰባሰብ የተለያዩ የአካልና የመንፈስ ሰቆቃ የሚፈጽሙበት ቦታ ነበር። በንጉሱ ግዜ ማእከላዊ ምርመራ በደርግ ግዜ የተፈጸመውን አይነት ግፍና ስቃይ በእስረኛ ላይ የሚፈጸምበት ቦታ አልነበረም። ለራሳቸው ክብር የነበራቸው የንጉሱ ዘመን ዳኞች እስረኛን በማሰቃየት የተገኘን መረጃ ውድቅ የሚያደርጉ ስለነበሩ መርማሪዎች ሰው አሰቃይተው በሚያገኙት መረጃ የሚያገኙት ጥቅም ስላልነበረ ግርፋትና ዱላ ዋንኛው የመመርመሪያው ዘዴ አልነበረም። ማእከላዊ ምርመራ በስቃይ ቦታነት ዝናው የገነነው በደርግ ዘመን ነው። በማእከላዊ ምርመራ ውስጥ በደርግ ዘመን በሃገሪቱ ዜጎች ላይ በተለይ በምሁራኑና በወጣት ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግፍ እዚህ መዘርዘሩ አያስፈልግም። እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ ነበር። የአጼ ሃይለስላሴ መንግስት ወድቆ የደርግ መንግስት ስልጣን ሲይዝ የማእከላዊ ምርመራ መርማሪዎች ወደ አዲሱ መንግስት መርማሪነት ተሸጋገሩ። እነዚህ እዛው የቀሩት መርማሪዎች የደርጉን ስርአት የመርማሪነት መስፈርት በማሟላት ደርግ የሚፈልገውን በማሰቃየትና በሰቆቃ ላይ የተመሰረተ ምርምራ ለማካሄድ ፈቃደኛ የነበሩ ናቸው። ለእንዲህ አይነቱ አሰራር ህሊናቸውን ማስገዛት ያልቻሉት ስራቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ። ደርግ ወድቆ ወያኔ ስልጣን ሲይዝ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል

በማእከላዊ ምርመራ ህዝብ በመግረፍና በማሰቃየት የታወቁት ጥቂት ግለሰቦች በአደባባይ ስማቸው ተጠርቶ ወህኒ ቢወርዱም ደርግ እንዳደረገው ሁሉ ወያኔም ቀድሞ ከነበረው ስርአት የወረሳቸው መርማሪዎች አሉት። ጥቂቶቹ ዛሬ ወያኔ በማእከላዊ ምርመራ ለሚፈጽመው ሰቆቃ “በባለሙያነት” እያገለገሉ ናቸው። የአሁኑን የማእከላዊ ምርመራ በተከታታይ መጥተው ካለፉት መንግስታትና ዘመናት የሚለየው የምርመራ ተቋሙን በከፍተኛ ደረጃ የሚመሩት ግለሰቦች በሙሉ ከአንድ የትግራይ ዘር የተውጣጡ መሆናቸው ዋንኛው ነው። ተቋሙ ዘረኛ በሆነ ለመጀመሪያ ግዜ የተደራጀው በዘመነ ወያኔ መሆኑ ነው።

 

6ይህን ሪፖርት ባጠናቀርኩበት ወቅት በዚህ የማሰቃያ ማእከል በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች በዚህ ምድር ላይ ይሆናል ተብሎ የማይጠበቅ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ነበር። በዚህ የማሰቃያ ቦታ የኦሮሞና የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅቶች አባላት ናችሁ ተብለው እጅግ አሰቃቂ ግፍ የተፈጸመባቸው እስረኖች ይገኛሉ። አንድ አቶ ሃሰን የሚባል ከደጋሃቡር ታፍኖ የመጣ የኦጋዴን ዝርያ ያለው እስረኛ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ከሁለት አመት በላይ ታስሮ ይገኛል። ጭራሹኑ ፍርድ ቤት ቀርቦ አያውቅም። ስድስት ወራት ሙሉ እጁ በካቴና፤ እግሩ በእግር ብረት ታስሮ ነው የቆየው። በድብደባ ብዛት የግራ ዘር ፍሬው /ብልቱ/ አንዱ ሟሙቶ ጠፍቷል። እንደ ከብት የወንድን ልጅ ብልት በመቀጥቀጥ ዘር አልባ ማድረግ በዛ ክፉ በሚባለው የደርግ ግዜ እንኳን ያልነበረ ነበር። በወያኔ ዘመን ግን ይህ የማሰቃያ ዘዴ በስፋት

እየተሰራበት ነው። ከምርጫ 97 በኋላ በተለይ በአማራ ክልል ውስጥ የቅንጅት ጠንካራ ደጋፊ የነበሩ ገበሬዎችን የወያኔ ካድሬዎች ሱሪያቸውን እያስወለቁ ብልታቸውን ይቀጥቅጧቸው ነበር የሚል ዜና ሲሰማ ብዙዎች ለማመን ይቸገሩ ነበር። በወያኔ እስር ቤቶች የሚካሄደውን ጉድ በአይኑ መመልከት፤ በጆሮው መስማት የዘወትር ውሎው ለሆነው እኔን ለመሰለውና በስር ቤቶች አካባቢ ለሚሰራው ሁሉ ግን አስገራሚ አይደለም። እኔ በተለይ እዚህ ማእከላዊ እስር ቤት በበርካታ የሃገሪቱ ዜጎች ላይ ሲፈጸም

እያየሁት ነው። ይህ ሃሰን የተባለ የኦጋዴን ሰው በኤሌክትሪክ መላ ሰውነቱ ተጠብሷል። አንዳንዴ ሳስበው ይህ ሰው በሳይንስ ላብራቶሪ ሰንዱቅ ውስጥ ተቆልፎባቸው አዲስ መድሃኒት እንደሚሞከርባቸው አይጦች ቆ ጥረውት ይሆን ወይ ያሰኘናል።

የዘረኛዎቹ የወያኔ ባለስልጣናት እንደ አይጥ ቆ ጥረው የማሰቃያ ጥበብን የሚመራመሩት በአቶ ሃሰን ብቻ አይደለም። ከነቀምት፣ ከአምቦ፣ ከምስራቅ ሀረርጌ እና ከከሚሴ ታፍነው መጥተው ማእከላዊ ምርመራ ጣቢያ ከ6 ወራት በላይ ከፍተኛ ስቃይ ስለደረሰባቸው ወገኖቼ ሳስብ ሃዘኔ ይበረታል። እነዚህ 12 የኦሮሞ ዝርያ ያላቸው ወጣቶች ናቸው። እጃቸው በካቴና ታስሮ በግድግዳ ላይ ይሰቀላሉ፣ይዘቀዘቃሉ፣ በኤሌክትሪክ ይገረፋሉ። ከነዚህ መሃል ሶስቱ ብልታቸው ላይ በደረሰባቸው ግርፋት ምክንያት ሽንታቸውን መቆጣጠር አይችሉም። አንዳንዶቹ ብልታቸው ላይ በደረሰባቸው ግርፋት የተነሳ ተኮላሽተዋል። አንዳንዶቹ አካላቸው ጎድሏል፤ አይናቸው ጠፍቷል፤ እጃቸው ተሰብሯል፤ ጥፍራቸው ተነቅሏል። ከአስራ ሶስቱ መሃል ሁለቱ በሰርጋቸው እለት ነው የታፈኑት። ከእነዚህም ሌላ እጃቸውንና እግራቸውን በካቴና ታስረው ቀንም ለሊትም በጨለማ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እዛው እስር ቤት ውስጥ የሚኖሩት ሁለት እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች አሉ።

በ1987 አመተ ምህረት በግብጹ መሪ ግድያ ሙከራ ላይ ተሳትፈዋል ከተባሉት ሶስቱ አንዱ እዛው በህመም ሲሞት ሁለቱ እስከ አሁን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ማእከላዊ እንደታሰሩ ናቸው። ከ15 አመት በላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ማለት ነው። እንግዲህ የግንቦት ሰባት ተከሳሾች እየተባሉ የሚጠሩት እስረኞች ከተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞችና ክልሎች ተሰባስበው የታጎሩት እንዲህ አይነቱ ግፍና ሰቆቃ በሚፈጸምበት፣ የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የወያኔ አባላት ፍጹም ዘረኛ ቁጥጥር ስር ባለ የምርመራ

ጣቢያ ውስጥ ነው። እጣቸው ምን ይሆናል ለሚለው ጥያቄያችሁ ከእስረኞቹ መሃል የጥቂቶቹን

ምርመራ በሚመለከት ያጠናቀርኩትን ዘገባ እነሆ ። በቅድሚያ ግን ላለመደጋገም በሁሉም ላይ በጋራ

የተፈጸመውን ላስቀድም።

6. በግንቦት 7 ተከሳሾች ላይ ስለተፈጸሙ ሰቆቃዎች

7

a. ሀ) በሁሉም የግንቦት ሰባት ተከሳሾች ላይ የተፈጸሙ ሰቆቃዎች

ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በርካታ ታሳሪዎች እጃቸው የተያዘው ሚያዝያ 16 2001 ነው።

የታሳሪዎቹ ብዛት በመጨረሻ ተከሰው ፍርድ ቤት በአካል ከቀረቡት 37 ሰዎች እጅግ የላቀ

ነው። እንደ ኮሎኔል የሺዋስ አይነቱ በድለላና በፍቃደኛነት፤ ገበያው አይችሉህም አይነቶቹ

በድብደባ ብዛት በጓደኞቻቸው ላይ መስካሪ ሆነው ለመቅረብ ፈቃደኛ በመሆናቸው ሚያዝያ

16 2001 ከታሰሩት መሃል የተለቀቁም አሉ። ሚያዝያ 16 2001 ከተያዙት በተጨማሪ ለወያኔ

መስካሪ ለመሆን በተስማሙት ሰዎች ጥቆማ የተያዙ እየተባለ ወያኔ በተለይ በሰራዊቱ ውስጥ

ራሱ የሚጠረጥራቸውን የአማራ መኮንኖች እና ፖሊሶች እስከ ግንቦት 2001 የመጀመሪያ

ሳምንት ድረስ ሲያስር ነበር። ለምሳሌ ከሃረር ተይዘው የመጡት ወታደራዊ መኮንኖች 13ኛ

ተከሳሸ ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣ 6ኛ ተከሳሽ ሌ/ኮ አበረ 7ኛ ተከሳሽ ሌ/ኮ አለሙ ጌትነት የተያዙት

ሚያዚያ 21 ቀን ነው። ጥቂት ሰዎች የግንቦት ወር መጀመሪያ ገደማ ታስረዋል። ሁሉም

ታሳሪዎች ማእከላዊ ምርመራ ግቢ ሲደርሱ እጃቸው በካቴና ታስሮ አይናቸው በጨርቅ

ተሸፍኖ እየተጎተቱ ነው ወደ ተዘጋጁላቸው የእስር ክፍሎች የተወሰዱት። የተወሰኑት በጋራ

በአንድ ክፍል ውስጥ የታሰሩ ሲሆን ወያኔ በከፍተኛ ጥላቻ የሚመለከታቸው ግን ተለይተው

ለብቻቸው በጠባብ ክፍል ውስጥ ታስረው እንዲቆዩ ተደርጓል። የእስረኞችን የምግብና

የመኝታ ሁኔታ እዚህ ማንሳቱ በሚቀጥሉት ቀናት ከተፈጸሙባቸው ግፍ ጋር ሲወዳደር ቅንጦት ስለሚመስል ማለፉን መርጫለሁ። እህል ውሃ እንዳይቀምሱ ተደርገው ለቀናት የታሰሩ እንደበረዶ በሚቀዘቅዝ የሲሚንቶ ወለል ላይ በለበሱት የቀን ልብስ ውለው እንዲያድሩ

የተደረጉ እስረኞች ነበሩ። እስረኞቹ በሙሉ በተያዙ በጥቂት ቀናት ወስጥ እጃቸው በካቴና

እየታሰረ አይናቸው በጨርቅ እየተሸፈነ ማንንም ማየት በማይችሉበትና ማንም እንዳያያቸው

በሸራ በተሸፈነ መኪና ለማእከላዊ ምርመራ ቅርበት ባለው የአራዳ ጊዮርጊስ አንደኛ ችሎት

ፍርድ ቤት እየቀረቡ ፖሊስ የምርመራ ስራውን እስኪጨርስ በእስር እንዲቆዩ

እየተወሰነባቸው ወደ ማእከላዊ ምርመራ ተመልሰዋል። በእነዚህ እስረኞች ላይ የተካሄደው

ትልቁና ዋናው አሰቃቂ ሰቆቃ የተፈጸመው ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ በሰጠው የምርመራ ጊዜ ውስጥ ነው። እነዚህ ተከሳሾች እስር ቤት ከታጎሩበት ቀን ጀምሮ የሚደርስባቸውን ግፍ እና የምርመራ ሂደት ጋር በቅርበት የምናውቀው ሰዎች እንደተረዳነው የጸረ- ሽብር መስሪያ ቤቱ ሊፈጸም ነበር ብሎ ላቀረበው መንግስት የመገልበጥ ከፍተኛ የሽብር ሙከራ አንድን ነጻ ፍርድ ቤት ሊያሳምን የሚችል ምንም አይነት መረጃ በጁ ያልነበረው መሆኑን ነው።

 

በቴሌቪዝን የቀረቡት ሰባራ ክላሽኖች ከመሳሪያ ነጋዴዎች እጅ የተያዙ እዛው ማእከላዊ ምርመራ ለረጅም ግዜ በኤግዚቢትነት ተቀምጠው የነበሩ ሲሆን የተቀሩትም ከወታደራዊ መኮንኖቹ በተለይ ለጀነራል ተፈራ ማሞ መንግስት እራሱ ለራሳቸው ጥበቃ የሰጣቸው ከላሽኖችና ሸጉጦች ሲሆኑ ከዛም ውጭ የቀረቡት መሳሪያዎች እራሱ ወያኔ ለሲቪል ታሳሪዎች ከ16 አመት በፊት ማመልከቻ አስገብተው ፈቃድ የሰጠባቸው ነበሩ።

 

ከነዚህ መሃል ማእከላዊ ምርመራ ለወንጀል ማስፈጸሚያ የተከማቹ በማለት ያቀረባቸው ከ83 አመቱ ከአቶ ጽጌ ሃብተማሪያም ተገኙ ያላቸው አንድ ኮልት 38ና አንድ ታጣፊ ክላሽን አዛውንቱ ከአንድ አቶ ገብረ መድህን ከሚባል የትግራይ ተወላጅ ላይ የደርግ መንግስት ሊወድቅ አካባቢ በ4800 ብር ገዝተው ለራስና ንብረት መጠበቂያነት በራሱ በመንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው የያዙት ለመሆኑ ከነፈቃዱ

ማእከላዊ ምርመራ እንደተመዘገበ ነው የመፈንቅለ መንግስት መሳሪያ ተብሎ በቴሌቪዠን

የቀረበው። በሌላም መልኩ አንዱ እስረኛ ከሌላው ጋር ሲነጋገር እንደነበርና ምን እንደተባባለ

የሚያስረዳ በድምጽ የተቀረጸ መረጃ ማቅረብ አልተቻለም። ታሳሪዎቹ አንዳቸው ላንዳቸው፣

ጀነራል ተፈራ 50 ግዜ ለጀነራል አሳምነው፣ ጀነራል አሳምነው 15 ግዜ ለኮሎኔል ደምሰው

8 ደውለዋል፤ የሚል የስልክ ቁጥርና የደወል ብዛት ካልሆነ በስተቀር ሰዎቹ ደውለው ይህን

ተነጋገሩ የሚል በድምጽ የተቀረጸ መረጃ ማእከላዊ ምርመራ ሊያቀርብ አልቻለም።

በቴሌቪዝን የቀረበው የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው

ከታሰሩ በኋላም ፍርድ ቤቱ በነጻ ከለቀቃቸው አቶ ጌቱ ወልዴ የተባሉ ነጋዴ ታሳሪ እጅ

የተያዘ ነበር። አቶ ጌቱ በወቅቱ ገንዘቡ ከየትና እንዴት በጃቸው ሊገባ እንደቻለ በቂ ምላሸ

የሰጡበት ጉዳይ ነበር። ከዚህ ውጭ በማስረጃነት የቀረቡት የመገናኛ መሳሪያዎች ለወንጀል

መፈጸሚያነት ለመዘጋጀታቸው መርማሪዎቹ እንኳን አንድን ነጻ ፍርድ ቤት ቀርቶ በወያኔ

ካድሬዎች የተሞላን ፍርድ ቤት ማሳመን የሚችሉ አልነበሩም። ሁለት የሳተላይት ቴሌፎኖችና አንድ የሳተላይት ኢንተርኔት መገናኛ ከሰዎች እጅ አገኘሁ ብሎ መፈንቅለ መንግስትን ለሚያክል ትልቅ ነገር ተዘጋጅተው የነበሩ የመገናኛ መሳሪያዎች በማለት እነዚህን መሳሪያዎች ማቅረብ የሚያስቅ ነው። በዚህ ላይም የስርአቱን የውሸት መረጃ የማቅረብ ልምድ ለምናውቀው ሰዎች፣ እውን እነዚህም የተባሉት እቃዎች በታሳሪዎቹ እጅ ነበሩ ወይስ ወያኔ

እንደለመደው ራሱ በታማኞቹ አማካይነት በየታሳሪዎቹ ቤት እያስቀመጠ አገኘሁት አለ የሚል

ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ማእከላዊ ምርመራ በመረጃነት ያቀረባቸው ሰነዶችም ማንም ሰው

በቀላሉ ሊያገኛቸው የሚችል በአብዛኛው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ዜጋ፣ በራሳቸው

በመርማሪዎቹና በአለቆቻቸው ቤት የሚገኙ ጽሁፎች ናቸው። ግንቦት ሰባት ያወጣውን

ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የዶክተር ብርሃኑን ንግግሮች፤ የግንቦት7 ን ድርጀታዊ መርሃ ግብር፤

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ድረገጾች ላይ የወጡ መንግስትን የሚቃወሙ ጸሁፎች

በግለሰቦች ቤት መገኘታቸው ለመፈንቅለ መንግስት መዘጋጀታቸውን ያሳያል በሚል

በመረጃነት ቀርቧል። ይሁንና መርማሪዎቹ ሌላው ሁሉ ቀርቶ የፈለጉትን ለማስፈጸም

በሚችሉበት በወያኔ ካድሬዎች በተሞላ ፍርድ ቤት እነዚህን መረጃዎች ይዞ መሄድ

ያስፈራቸው በመሆኑ እስረኞቹን ወንጀለኛ ለማድረግ ጉዋደኞቻቸው እንዲመሰክሩባቸው

ወይም ራሳቸው ታሳሪዎቹ የራሳቸውን ወንጀለኛነት እንዲያምኑ ማድረግ ነበረባቸው።

የታሳሪዎቹ ስቃይ የሚጀምረው መርማሪዎቹ የሚፈልጉትን በሙሉ በሰው ምስክርነት ወይም በታሳሪዎቹ የእምነት ቃል ለማስደገፍ በሰሩት የግፍ ስራ ነው።

በቅድሚያ መርማሪዎቹ በቀላሉ ሊሰበሩና የምንፈልገውን ይሰጡናል ያሉዋቸውን ታሳሪዎች

በመለየት በድለላና በዱላ በተቀሩት እስረኞች ላይ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎች አሰባሰቡ። ከዛ

በኋላ ፊታቸውን ያዞሩት በተቀሩት እስረኞች ላይ ነበር። እያንዳንዱ እስረኛ ከምሸቱ 2 ሰአት

ጀምሮ እስከ ውድቅት ድረስ ባለው ግዜ ከታሰረበት ክፍል እጁ በካቴና አይኑን በጨርቅ

እየታሰረ ተወስዶ ፊታቸውን በማያያቸው መርማሪዎች ፊት የሰራው ወንጀል ምን እንደሆነ፣

ለተሰራው ወንጀል መርማሪዎቹ በቂ ማስረጃ እንዳሰባሰቡ ስለዚህም ሌላ መከራ ውስጥ

ከመግባቱ በፊት ጥፋተኛነቱን አምኖ የእምነት ቃሉን እንዲሰጥ ይገደድ ነበር። በመጨረሻ

ለፍርድ ከቀረቡት ታሳሪዎቹ መሃል የመርማሪዎቹን ምክር አዘል ማስፈራሪያና ዛቻ ሰምቶ

ጥፋተኛ ነኝ ያለ አንድም እስረኛ አልተገኘም። ይህ የማስፈራራትና የማግባባት ስራ የትም

እንደማያደርስ የተረዱት መርማሪዎች ወደ ሌላው የማሳመኛ ምእራፍ የተሸጋገሩት ከዚህ በኋላ ነው። አብዛኞቹ እስረኞች በማእከላዊ ምርመራ ያሳለፏቸው 45 የስቃይ ቀናት ግርፋቱ፣

ስቅላቱ፣ የአካልና የመንፈስ ሰቆቃው ተጀመረ። ለአብነት ያህል በተወሰኑት ታሳሪዎች ላይ

የደረሰውን ግፍ ከዚህ በታች ለመዘርዘር ሞክሬአለሁ።

ለ) 16ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ አባቡ ተፈሪ

 

9 መቶ አለቃ አባቡ ተፈሪ የተያዘው ባህር ዳር ከተማ ከሌሎች 16 ሰዎች ጋር ነው። በዚህ ሰው ላይና አብረውት ወደ ማእከላዊ በተላኩት ተጨማሪ 10 እስረኞች ላይ ቅጥቀጣ የተጀመረው ማእከላዊ መምሪያ ከመድረሳቸው በፊት እዛው ባህር ዳር ውስጥ መ.ኮ.ድ ተብሎ በሚጠራው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ነበር። እስረኞቹ ከባህር ዳር መ.ኮ.ድ ወታደራዊ ካምፕ በካቴና ታስረው ግንቦት 10 ቀን 2001 አመተ ምህረት ማእከላዊ ምርመራ ሲገቡ ፊታቸው የቆሰለ፣ያበጠ አይናቸው ደም የሚያነባ፣ መራመድ አቅቶአቸው የሚያነክሱ ነበሩ። መቶ አለቃ አባቡ ማእከላዊ በደረሰ በማግስቱ ምሽት ላይ ነው በማእከላዊ ምርመራ መርማሪዎች እየተደበደበ ወንጀሉን እንዲያምን ጥያቄ ይቀረብለት የነበረው። እጁን በካቴና እየታሰረ አይኑን ተሸፍኖ በብረት ማንጠልጠያ ላይ በወፌ ላላ እስር ታስሮ ውስጥ እግሩን ተገርፏል። ልብሱን በሙሉ አውልቆ መሬት ላይ እንዲተኛ እየተደረገ የስቃይ ጩኸቱ ለገራፊዎቹና ለሌላም ሰው ጆሮ እንዳይደርስ አፉ በገማ ጨርቅ እየተጠቀጠቀ ጭንቅላቱን እጆቹን ጣቶቹን ታፋውን ሽንጡን በዱላ ሲቀጠቀጥ በኤሌትሪክ ገመድ እየተገረፈና በእርግጫ እየተመታ ለቀናት ተሰቃይቷል።

 

ይህ እስረኛ እንደሌሎቹ እስረኞች አይኑን እንደተሸፈነ መርማሪዎቹ ወንበር ላይ አስቀምጠው

እየተገባበዙ ባሳረፉበት ጥፊ ብዛት ጆሮው ለረጅም ግዜ ታሞ የነበረ ሲሆን አሁንም አንድ

ጆሮው ታማሚ ሆኖ ቀርቶአል። መቶ አለቃ አባቡ ተፈሪ በማእከላዊ መርማሪዎች እጅ ስቃዩን በሚያይበት ወቅት በተለይ መርማሪዎቹ መሃል አማራ የሆነ ሰው በሌለባቸው ወቅቶች የትግራይ ተወላጆች መርማሪዎች ዘረኛ የስድብ ጎርፍ ይወርድበት ነበር። ዘሩን በመጥቀስ “ግም አማራ”፤ “ብስብስ አማራ”፣ “አማራ ሽንታም መሆኑን አታውቅም እንዴ?” “እዚህ አንተን ብንጠብስህ ሽታው ለአማራ ህዝብ የሚደርሰው ይመስልሃል?”፤ “በኛ እጅ የገባና ኤድስ የያዘው አንድ ነው”፤ “በኤድስ ቫይረስ የተሞላ ደም እንድንወጋህ ትፈልጋለህ?” “አንተን እዚህ ልንደፋህ እንችላለን፣ የፈለግንበት ወስደን እሬሳህን መጣል እንችላለን የሚጠይቀን የለም” የሚሉ ስብእናውን የሚነኩ አእምሮውን የሚያውኩ የስነ ልቦና ሰቆቃ ጭምር ተፈጽሞበታል።ይህ እስረኛ ለረጅም ቀናት ያለማቋረጥ በተካሄደበት ስቃይ የተነሳ በመጨረሻ መርማሪዎቹ

የፈለጉትን በሙሉ ፈርሞላቸውል። ለዚህ ድል የበቁት መርማሪዎች ሰውየውን መስበር

በመቻላቸው ሲመሰጋገኑ ሲፈነድቁ ማእከላዊ ምርመራ አልበቃ ብሏቸው እንደነበር

ይታወቃል።

ሐ) 30ኛ ተከሳሽ ም/ሳጅን ጎበና በላይ

በዚህ እስረኛ ላይም ከላይ በአስረኛው ተከሳሽ ላይ የደረሰው የአካልና የመንፈስ ሰቆቃ

ደርሶበታል። በሌሊት እየተወሰደ እንደእባብ ይቀጠቀጥ ነበር። በኤሌክትሪክ ገመድ ተገርፏል

በኤሌትሪክ ሃይል ተቃጥሏል። ተሰቅሎና ተዘቅዝቆ ተገርፏል። ልብሱን በሙሉ የውስጥ

ሱሪውን ሳይቀር እንዲያወልቅ ተደርጎ መርማሪዎቹ እየተፈራረቁ ቆዳው እስኪላጥ

ገርፈውታል። የጋይንት ሰው መሆኑን መሳለቂያ በማድረግ “ከሃምሳ ጋይንት አንድ አጋንንት

ይሻላል፣ አንተ ሆዳም ጋይንቴ” የሚሉ ስድቦችን እያወረዱ ሌሎችንም አጸያፊ ክብርና ስብእና

ነክ ስድቦች እየተሳደቡ ያዋርዱት እንደነበር ለማወቅ ችያለሁ። ይህ ሁሉ ሰቆቃ የተፈጸመው

መርማሪዎቹ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያምንላቸው ነው። ለመወንጀል የሚፈልጓቸውን ሰዎች እንዲወነጅልላቸው ነበር። ሳጅን ጎበና ለበርካታ ምሽቶች ያለማቋረጥ በደረሰበት ግርፋትና ስቃይ በመጨረሻ ተሸነፈ። መርማሪዎቹ ጽፈው ያቀረቡለትን ቃሌ ነው ብሎ ፈረመ። ይህ መረጃ ነው በፍርድ ቤት ራሱንም ሆነ ሌሎችንም ባልደረቦቹን ለእድሜ ልክ እስራት 10 የዳረጋቸው። በሳጅን ጎበና እና በሌሎችም እስረኞች ላይ ምርመራ እንዲያደርጉ ከተመደቡ በርካታ መርማሪዎች መሃል እስረኞቹን በተለያየ ደረጃ ሲያሰቃዩ የነበሩት 10 መርማሪዎች

ናቸው። ከነዚህ 10 መርማሪዎች መሃል የተለየ ጭካኔ በመፈጸም የሚታወቁ አሉ። ከነዚህ

መርማሪዎች ጋር እየተመሳጠረ ተመርማሪዎቹ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ዱላ ከሰውነታቸው

ላይ እየተመለከተ፤ ቃላቸውን ተገደው እየሰጡ እንደሆነ እያወቀ፤ በፈቃደኛነት የሰጡት ቃል

ነው እያለ ምስክርነቱን በመስጠት የመርማሪዎቹን ህገ ወጥ ሰነድ ህጋዊ በማድረግ

የመርማሪዎቹን ስራ እንዲያቀል የተመደበ ዳኛም ነበር። የእነዚህን ጨካኝ መርማሪዎችና

የዳኛውን ስም ዝርዝር በዘገባው መጨረሻ አቀርባለሁ።

 

መ)12ኛ ተከሳሽ ኮለኔል ፋንታሁን ሙሃባ ሙፍቲ ይህ እስረኛ የተያዘው ሚያዝያ 16 ትግራይ ክልል ምእራብ ዞን ሽሬ ማእከላዊ እዝ ካምፕ ውስጥ ነው። ቢሮው ውስጥ ተቀምጦ ስራውን እየሰራ በነበረበት ወቅት ነበር ክብሪት በሚባል ቅጽል ስሙ በሚታወቀው በኮሎኔል ደሳለኝ ወደ አስተዳደር ቢሮ ተጠርቶ በፈቃዱ ሄዶ ነው እጅ ወደላይ የተባለው። ሚያዚያ 22 2001 አ. ም ማእከላዊ ምርመራ ሲደርስ ከመንገድ ድካምና በፊቱ ላይ ከሚነበበው ጭንቀት በስተቀር እንደሌሎቹ ከሌሎች ቦታዎች እንደመጡት

እስረኞች ፊት ለፊት የሚታይ የአካል ጉዳት አልነበረበትም። በኮሎኔል ፋንታሁን ላይ ቅጥቀጣ የተጀመረው ሚያዝያ 23 2001 አ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለተከሰሰበት ክስ ቃሉን እንዲሰጥ ሲጠየቅ ክሱ ሁሉ ሃሰት ነው ብሎ መልስ በሰጠበት እለት ምሽት ነው። ከምሽቱ አራት ሰአት ላይ በጨለማ አይኑን በጨርቅ ተሸፍኖና እጁን በካቴና ታስሮ እንደበግ

እየተጎተተ ተወሰደ። በዛን እለት ለማታው የምርመራ ስራ መርማሪዎች ቁጥራቸው በዛ ብሎ

ተመደበ። ኮሎኔሉ ጥጋበኛ እንደሆነና ጥጋቡን ማስተንፈስ እንደሚገባ መመሪያ ተሰጥቷቸው

ነው አምስት መርማሪዎች የተመደቡለት። የሚገባው ቋንቋ ዱላ ነውና በሚገባው ቋንቋ

አናግሩት የሚለው መመሪያ የተሰጠው በወቅቱ የማእከላዊ ምርመራ ዋና ሃላፊ በነበረው ታደሰ መሰረት በተባለው የለየለት ጨካኝና ዘረኛ የሆነ የትግራይ ተወላጅ የወያኔ ባለስልጣን ነው።ኮሎኔል ፋንታሁን ማእከላዊ ምርምራ ካሳላፋቸው በርካታ ምሽቶች ውስጥ አብዛኛው እስረኛ

ሲተኛ እርሱ ሲሰቀል፣ ሲዘቀዘቅ፣ ሲገረፍ በዚህም ምድር ላይ ሰው ይችለዋል ተብሎ

የማይገመት ስቃይ ሲወርድበት ነበር። ኮሎኔሉ ላይ በድብደባ የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ

በመሆኑ እዛው እስር ቤት ውስጥ እያከሙ ይደበድቡት ነበር። በመጨረሻም እርሱም

እንደሌሎቹ እስረኞች መርማሪዎቹ የፈለጉትን ፈርሞ ከአካላዊ ስቃይ ተገላግሏል።

 

 

ሠ) 22ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ

በማእከላዊ ምርመራ የተመደቡ ገራፊዎች እናትና እህት የሌላቸው ይመስል በዚች የሶስት

ልጆች እናትና የአንድ ልጅ አያት ለመሆን በበቃች ሴት ላይ የፈጸሙት ግፍ እጅግ ዘግናኝ

ነው። እንደሌሎቹ ግፉ በእማዋይሽ ላይ የሚፈጸመው ሌሊት ላይ ነው። እነደሌሎቹ አይኗ

በጨርቅ ተሸፍኖ እጇ በካቴና ታስሮ ነበር ለምርመራ የምትወሰደው። እየሰቀሉ የውስጥ

እግሯን እጆቹዋና ታፋዋን መቀመጫዋን ጀርባዋን በቃላት ለመግለጽ በሚቸግር ጭካኔ

ገርፈዋታል። መርማሪዎቹ የሰዎችን ስም እየጠሩና ፎቶግራፍ እያሳዩ ከነዚህ ሰዎች ጋር

ተሰብስበሻል፣ ታውቂያቸዋለሽ ይህን እመኚ በነሱ ላይ ለመመስከር እሺ በይን እያሉ ነበር

እማዋይሽን የሚገርፏት። በእማዋይሽ ላይ ከደረሰው አሰቃቂ ግርፋት ግን ልብሷን አስወልቀው 11 ጡቷ እስከሚደማ ድረስ በኤሌክትሪክ ገመድ የገረፏት መሆኑ ነው። ይህች ሴት በጡቷ ላይ የደረሰባት ግርፋት የቀሰቀሰው ስቃይ እና ህመም ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ከወረደች በኋላም አልቆመም። የምትኖረው ስቃይ ማስታገሻ ኪኒን እየዋጠች እንደሆነ ከማረሚያ ቤቱ ያሰባሰብኩት መረጃ ያሳያል። ወ/ሮ እማዋይሽም ስቃዩን ለማስቆም ገራፊዎቿ የፈለጉትን ፈርማለች።

 

ረ) 36ኛ ተከሳሽ አቶ ጌቱ ወርቁ

አቶ ጌቱ ወርቁ ከሌሎቹ እስረኛ የሚለየው አማራ አለመሆኑ ነው። የዶክተር ብርሃኑ የቅርብ

ዘመድ ነው። በማእከላዊ ምርመራ በእዚህ እስረኛ ላይ የተያዘ መረጃ የለም። ክሱ ግን

ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን የሽብር ስራ ለመስራት ማሴር ነው። ይህ እስረኛ እንደሌሎቹ

ሁሉ ተመሳሳይ ቅጥቀጣ ተፈጽሞበታል። ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው ከብዙ ድብደባ በሁዋላ

ተዝለፍልፎ በወደቀበት ወቅት ገራፊዎቹ ከወደቀበት አንስተው በካቴና በታሰረው እጁ ለ19

ሰአታት የሰቀሉት መሆኑ ነው። አዎን “አንድ ሰው እንዴት ለ19 ሰአት ይሰቀላል?” ትሉ

ይሆናል። ይህ የተጋነነ ወይም የተሳሳተ መረጃ አይደለም። የአቶ ጌቱ መርማሪዎች ሌሊት

ሲገርፉት ቆይተው ምንም ማግኘት ሳይችሉ ሲቀሩ በዛው ምሽት ሰቅለውት በሩን ዘግተው

ወጥተው ሄደዋል። በማግስቱ ከሰአት በኋላ ነው በሩን ከፍተው አቶ ጌቱን ከሰቀሉበት

ያወረዱት። ይህ እስረኛ በተሰቀለበት ቦታ እጁ በካቴናው ተቀርድዶ ይፈሰው የነበረው ደም

ወለሉን ሞልቶት እንደነበር መረጃ አሰባስቤአለሁ። አቶ ጌቱ የደረሰበት ስቃይ እጅግ አሰቃቂና

ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለበት በመሆኑ ወደ ሽንት ቤት መሄድም ሆነ ሽንት ቤት መቀመጥ

ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ከዚህም የተነሳ የእስር ባልደረቦቹ በሚውሉበትና

በሚተኙበት ክፍል በባልዲ ላይ በሰው ተደግፎ እየተቀመጠ እዛው ክፍል ውስጥ ይጸዳዳ

ነበር። አቶ ጌቱም በመጨረሻ መርማሪዎቹ የፈለጉትን ፈርሞ ግርፋቱ እንዲቆም አድርጓል።

 

ሰ) 6ኛ ተከሳሽ ሌ/ኮ አበረ አሰፋ

ሌ/ኮ አበረ አሰፋ የተያዘው ሚያዚያ 21 ሃረር ከተማ ውስጥ ነው። ከሁለት ከፍተኛ መኮንኖች

ጋር ሚያዘያ 23 ቀን ከቀኑ 6 ሰአት ሶስቱም መኮንኖች ማእከላዊ ምርመራ ሲገቡ እጃቸው

በካቴና ከመታሰሩና የለበሱት ልብስ የቆሸሸ ከመምሰሉ በስተቀር የሚታይባቸው የአካል ጉዳት

ወይም ጭንቀት አልነበረም። ሶስቱም ታሳሪዎች ቅዳሜ ሚያዝያ 24 2001 አ.ም

እንደተለመደው አራዳ 1ኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ተጠየቁ።

የቀረበብን መንግስት የመገልበጥ ሽብር የመፍጠር ክስ ሃሰት ነው ብለው አስተባበሉ። ፖሊስ

ማስረጃዬን ለማጠናቀር ታሳሪዎቹ በእስር እንዲቆዩ የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት

በድንቁርናዋና በታማኝነቷ ለተሾመችው ታሪኳ ለተባለችው የውሸት ዳኛ ጥያቄ አቀረበ።

ሁሌም እንደሚሆነው የፖሊስን ጥያቄ በተለይ በእንዲህ አይነቱ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ጉዳይ

ውድቅ የማድረግ ፍላጎትም ነጻነትም የሌላቸው ዳኞች እንደሚያደርጉት ሁሉ ታሪኳም

ተከሳሾቹ በስር ቆይተው ምርመራ ይደረግ የሚል ውሳኔ አስተላለፈች። ታሪኳም ሆነ

ሌሎችም ተመሳሳይ ውሳኔ የሚሰጡት ዳኞች በሙሉ ለፖሊስ የመረጃ ማሰባሰቢያ ቀጠሮ ቀን

ሲያራዝሙ ፖሊስ ምን እንደሚሰራበት ጠንቅቀው ያውቃሉ። የውሸት ምስክርና ማስረጃ

ማሰባሰቢያ ግዜ እየሰጡ እንደሆነ ያውቁታል። ታሳሪዎች ራሳቸውን ወንጀለኛ የሚያደርግ

ቃል በዱላና በግርፋት እንዲሰጡ ለማድረግ መርማሪዎቸ የሚፈልጉትን ግዜ እየፈቀዱ

12 እንደሆነ ያውቁታል። እነዚህ ዳኞች ከገራፊዎቹ ጋር ባንድ ክፍል ውስጥ ተገኝተው እስረኞች በጃቸው አይግረፉ እንጂ በእስረኛ ላይ የሚካሄደውን ሰቆቃ እያወቁ ፈቃድ የሚሰጡ

ከገራፊዎቹም በላይ በምድር በወንጀለኛነት፤ በሰማይ በሃጢያተኛነት አስከፊ ቅጣት ሊቀጡ

የሚገባቸው ናቸው። ይህች የአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት ዳኛ ሌ/ኮ አበረ ታስሮ

ምርመራ ይቀጥል ብላ በወሰነች በሁለተኛው ቀን ሚያዚያ 25 2001 ከምሽቱ 2. 30 ላይ

በሌ/ኮ አበረ ላይ ምርመራው ተጀመረ። በመጀመሪያ ማስፈራራት ቀጥሎ በወያኔዎች

የተለመደውን በዘር ላይ የተመሰረተ አማራነትን የሚያንቋሽሽ ስድብ እና ድንፋታ ቀጠለ።

ሌ/ኮ አበረን የመረመሩት መርማሪዎች የሌላ ዘር ያልተቀላቀለባቸው በታደሰ መሰረት

የተመደቡ የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። በኮ/ል አበረ ላይ ያለምንም ማመንታት የወረደው ለከት

የሌለው ብልግና የተቀላቀለበት እና የለየለት ጸረ -አማራ የሆነ ስድብ ገራፊዎቹ በሙሉ

የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸውና የተናገሩት የትም አይሰማም ከሚል የርስ በርስ መተማመን የመጣ ነበር። ያልገባቸው ነገር ቢኖር እነሱ በደም ፍላት የሚሳደቡት ስድብ ሰው ከሚገርፉበት ክፍል አልፎ ውጭ ለነበርነው ለሌሎች ሰዎች ጆሮ ይደርስ እንደነበር ነው። አሁን “በእንዲህ አይነቱ ሽንታም አማራ ነው በስንት ቆራጥ የትግራይ ጀግና ልጆች ያመጣነው ስርአት የሚናደው? አንተን ብቻ አይደለም ዘርማንዘርህን ቀሚስ አስለብሰን የወጥ ቤታችን ሰራተኛ አድርገን እንገዛዋለን” ይህን የመሰሉ ጸያፍና መዘዛቸውን በውል የማይረዱትን ስድብ ነበር አበረን ተሻግረው በአማራ ህዝብ ላይ ሲያወርዱ የነበረው። በማእከላዊ ምርመራ እንዲህ አይነቱ የወያኔ የዘረኛነት ብልግና በእነዚህ ዘረኞች እጅ በገባ ከየትኛውም ዘር በመጣ ታሳሪ ላይ የሚፈጸም ነው። እነዚህ ሰዎችና አለቃቸው መለስ ዜናዊ ህዝብን የብሄር ብሄረሰብ መብት እያሉ እያጭበረበሩ በሆዳቸው ግን አፍነው የያዙት ክርፋቱ እስከአድዋ የሚደርስ በሃገሪቱ ለሚገኙ ዘሮች በሙሉ ያላቸው ንቀት እንደሆነ በማእከላዊ ታስሮ በነዚህ መርማሪዎች እጅ የወደቀ የየትኛውም ብሄረሰብ ተወላጅ ያውቀዋል። ይህ እጅግ የሚያስደነግጥ ነገር ነው።

 

ከስድብ በኋላ በኮሎኔል አበረ ላይ የወረደው የዱላና ጥፊ መዓት ነው። “ህገ መንግስቱን

ለመናድ ሰው ስታደራጅ ነበር፤ እመን”ሲሉት “ህገመንግስት ለመናድ ሰው አላደራጀሁም፤

የተያዝኩት ከንግግራችሁም እንደምሰማው ለአማራነቴ ባላችሁ ጥላቻ ነው። የዘረኛ የጥቃት

ኢላማ እንጂ ወንጀለኛ አይደለሁም” አላቸው። የኢህዴን መስራችና አሁን የብአዴን ማእከላዊ

ኮሚቴ አባላት ሆነው መንግስት እየመሩ ነው የሚሏቸውን ሰዎችና ከፍተኛ መኮንኖች ስም

እየጠሩ “አይዟችሁ ግፉበት ይሏችሁ ነበር፣ እንዳይጋለጡም አንተ ብቻ እንድታገኛቸው

ይደረግ ነበር፤ ሁሉንም እናውቃለን