A visitor’s experience of Kilinto Prison today የቂሊንጦ “ውሎና እነካህሳይ

0
787

30-1-2016

በስንታየሁ ቸኮል

ጥር 20/5/08 በጠዋቱ መንገድ ጀመርኩ ምክንያቱ ደግሞ በእስር የሚሰቃዩ ጓዶችን ለመጠየቅ ወደ ቂሊንጦ ማጎሪያ ለመሄድ ነበር፡፡ ከሶስት ታክሲ
ማቆራረጥ በኃላ መግቢያው በር ላይ ደረስኩ የጥበቃ ተረኛ
ሁለት ሴቶች የተጠያቂ ሰዎች ስም እየመዘገቡ ነው፡፡
በወንዶች በኩል በምትመዘግበው አባል ለምዝገባ ተሰለፍኩ መልካም የሚባል ትህትና አላት ስሟ ሃናን ብለው ሲጠሯት ሰምቻለሁ ሃናን መታወቂያ ካየች በኃላ የተጠያቂው ስም
ጠየቀችኝ፡፡ ሀብታሙ አያሌው ብርሃኑ ተ/ያሬድ ዘላለም
ወርቃገኘሁ ፍቅረማሪያም አስማማው ኧረ.,, ብዙ ናቸው፡፡ እያልኩ በፍጥነት ስማቸውን
ደረደርኳቸው፡፡
ሃናን ,,ሀብታሙ እያለች ሳቀች
ምነው መጠየቅ አይቻልም? በማለት ጠየኳት
“መጠየቅ የሚቻለው በእንድ ዞን
ያሉትን ብቻ ነው አለች፡፡ እኔ የምጠይቃቸው በሁሉም ዞን ያሉ እስረኞችን ነው፡፡ አይፈቀደም? አልኳት,,
ታጋይ ሃናን እንደሱ አይቻልም፡፡ አንተ ከዚህ በፊት እዚህ መጥተህ ታውቃለህ? አለች፡፡
“አዎ,,,,,ቆየት ቢልም መጥቼ አውቃለሁ በማለት መለስኩላት)
ወታደር ሃናን ቆይ ጠብቅ አንድ ጊዜ በማለት ካህሳይ,,,,በማለት ተጣራች? በኮኮብ ማዕረግ ያሸበረቀ
አለቃ “ካህሳይ መጣ)))
ሃናን የምጠይቃቸውን ሰዎች ስማቸውን ነግራው መታወቂያውን ለካህሳይ ሰጠቺው፡፡ “ምን ተገኝቶ ይሆን በማለት ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡
ሃናን ወደ እኔ መጣች ካህሳይ የደህንነትነና ጥበቃ ሀላፊ ነው፡፡ “እሱ አይቶት አስገቡ ካለ ትገባለህ አለች) እኔም ተስፋ አድርጌ አለቃ ካህሳይ
የሚወስነውን በትህግስት መጠበቅ ጀመርኩ ከትንሽ ቆይታ በኃላ
አለቃ ካህሳይ መታወቂያውን ይዞ መጣ ኮስተር ባለ ፊቱ >እኛ ጋር
እስረኛ ጠይቀህ ታቃለህ? አለኝ፡፡ ከዚህ ቀደም
ጓደኞቼን ጠይቄ አውቃለሁ አልኩት >> አለቃ ካህሳይ እያየኝ መገለማመጥ ጀመረ፡፡ ግራ ገባኝ ምን ተገኘ
,, ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ፡፡
ሀብታሙ አያሌው ምንህ ነው? ብሎ ካህሳይ ጠየቀኝ፡፡ ጓደኛዬ ስል መለስኩለት
ፊቴን ማጨማደድ ጀመርኩ ምን ያመጣል ግፋ ቢል ቢከለክለኝ
ነው፡፡ በሚል ነበር አለቃ ካህሳይ ወታደር ሃናን ጠርቶ ከአንድ ሰው
በላይ መጠየቅ እንደማልችል ነገራት) ከረጅም መፋጠጥ በኃላ ተመዘገብኩ ከብዙ ሰዓት ቆይታ በኃላ
ወደ ውስጥ ገባው አለቃ ካህሳይ ከጀርባዬ ተከትሎኝ ገባ “ሂድ እዛ ጥግ ምጽላል የያዘውን እቃ ፈትሺው ሲል በእጁ እያሳየት>> ካህሳይ ንቀቱ ሌላ ነበር
ታጋይ ምጽላል የያዝኩት በሹካ በሳ በማድረግ ቀደደቺው ትንሽ ቅምስ?
በደንብ ቀመስኩ ሞባይል ወረቀት ከመታወቂያ ጋር ካስቀመጥኩ በኃላ
እስረኞች መግቢያ በር ላይ ሌላ ብርበራ አለ፡፡ ሶስት ፈርጣማ ወታደሮች ይፈትሻሉ ካህሳይ አሁንም ከኔ ጋር ጸብ ያለው ይመስላል፡፡
ወታደር መብራቱ ከፈታሾቹ አንዱ ነው፡፡ እሱን ፈትሸው አለ፡፡ ሲበዛ ሳቄ መጣ ልክ እንደ ቃሊቲ የቤተሰብ ማህበር ይመስላል፡፡ የአለቃ ካህሳይ ትህዛዝ ጠበቅ ያለበት መብራቱ እስከ ውስጥ ድረስ ፍተሻው አስገራሚ ነበር፡፡ የመብራቱን ፍተሻ
ከጨረስኩ በኃላ ወደ ዞን3 ግቢ ገባው፡፡ ሀብታሙ
አያሌው በአስጠሪዎቹ ተጠራ ሀብትሽ ቢጃማ እንደለበሰ መጣ ከእንቅልፉ እንደተነሳ ነው
ከሀብታሙ ጋር ከተገናኘን ቆየት ብያለሁ ጠበቅ ያለ
ሰላምታችንን እንደተለዋወጥን ሀብታሙ አይኑን በምልክት
እያሳየኝ ጠቀሰኝ ከግራ በኩል አንድ ሰው መነጽር አድርጎ ቆሟል፡፡ እኔ ጠያቂ
መስሎኝ ነበር ጠያቂ መስሎ የቆመው ሰው
ሀብትሽ ሲነግረኝ በግቢው የሚታወቅ ደህንነት
ነው፡፡ አንድ እስረኛ ሀብታሙ ጋር ተጠግቶ በጆሮው ስለ ቆመው ሹክ አለው፡፡ በጣም አቀዋለሁ ሲል ሀብታሙ መለሰለት ብዙ የምትገምተው አይደለም እዚህ ግባ የማይባል ደከም ያለ ነገር ነው፡፡ ከበር ስገባ ጀምሮ የጠያቂ ስም
ካስመዘገብኩ በኃላ የነበረውን ሁኔታ ሁሉንም ነገርኩት ሀብትሽ በጣም,,,
ሳቀ,,,ይገርማል ማንም ሰው ድጋሚ ቢመጣ ባይመጣ መታወቂያ
ካሰየ በቀጥታ መግባት ይችላል፡፡ አንተን ውጪ ያቆዩህ ይሄንን
ደህንነት እዚህ እስኪመድቡት ነው፡፡ ምን ያወራሉ በቃ ይሄንን ስጋት
ለመስማት ሲደክሙ ያሳፍራል፡፡ በንግግር የሚሸበር መንግስት
አስሮም ይሸበራል በማለት ሀብትሽ መረር ብሎ ተናገረ፡፡ ሀብታሙ
ጤናው እንዴት ነው? የሚሉ ወገኖች ቀላል አይደሉም፡፡ አሁን
እንዴት ነህ? ብዬ ጠየኩት፡፡
እግዚያብሔር ይመስገን እነሱ እንዳሰቡት በቀል
ቆሞ ለመሂድ እንኳን አልችልም ነበር፡፡ ከፍተኛ ጥቃት አድርሰውብኛል፡፡ ሀብትሽ የሆስፒታል ቀጠሮ ላይ መሆኑ ኩላሊቱ በጣም
እንደቆሰለ አወራኝ ስለ አንድነት ፓርቲ አንደኛ አመት ትንሽ ተጨውተን ሳንጨርስ
ሰዓት ሞላ ሀብታሙ መጨረሻ ላይ አንድነት አልፈረስ ይመለሳል፡፡ እያለ ወደ ውስጥ ገባ በአየር ላይ ሰላምታ ተለዋውጠን ተለያየን
በቀጣይ ወደሌሎች መሄዱ ይቀጥላል፡፡ በታሳሪዎች ዙሪያ የነጻነት ትግል ዋጋ አለው እያንዳንዱ ሰው ለነዚህ ወንድሞቻችንን
ቢያንስ የጥየቃ ጉብኝት በማድረግ ድጋፍና አጋርነታችንን እናረጋግጥ፡፡ ክብር ለታጋዮቻችን!!

Sourced from Sintayehu Chekol’s Facebook Page

[Google]