ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ባስመዘገበችው ስኬት ተሸለመች

0
475

01 Feb 2015

ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ባስመዘገበችው ስኬት ተሸለመች

አዲስ አበባ ጥር 23/2007 ኢትዮጵያ ወባን ጨምሮ በጤናው መስክ ባስመዘገበችው ስኬት የአፍሪካዊያን መሪዎች ወባ ጥምረት አመታዊ ሽልማት አገኘች።

13 የአፍሪካ አገራትም እውቅና አግኝተዋል።

የአፍሪካ መሪዎች ወባ ጥምረት ድርጅት/አልማ/በአውሮፓውያኑ 2014 ወባ በአፍሪካ በዜጎች ላይ የሚያደርሰውን የሞት፤የህመምና መሰል አደጋዎችን ለመከላከል እኤአ በ2009 መስከረም ወር በታንዛኒያ ዳሬሰላም የተቋቋመ ድርጅት ነው።

ደርጅቱ አፍሪካውያኑ አገሮች በጤናና ተያያየዥ ጉዳዮች ያከናወኑትን ተግባር በተመለከተ ያዘጋጀውን ሪፖርት አዲስ አበባ ውስጥ ይፋ አድርጓል።

አገሮቹ ወባን ለመከላከል ያከናወኑትን ተግባር በአለም የጤና ድርጅት፤በሲቪክ ማህበራትና በምሁራን መረጃው መሰብሰቡን ገልጿል።

ሪፖርቱ “ኢትዮጵያ በስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት፤በእናቶች ሞትና  በጨቅላ ህጻናት ሞት ቅነሳ ስኬታማ ስራ አከናውናለች” ሲል አትቷል።

ለዚህ ስኬቷም ድርጅቱ ያዘጋጀውን አመታዊ ሽልማት በቀዳሚነት ወስዳለች።

የተቋሙን ሽልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሮበርት ጋበሬል ሙጋቤ እጅ ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ “ኢትዮጵያ ለዚህ ስኬት የበቃችው ህብረተሰቡን ባሳተፈ እና በመከላከል ላይ የተመሰረተ የጤና ፖሊሲ በመከተሏ ነው” ብለዋል።

የአፍሪካ መሪዎች ወባ ጥምረት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሚስ ጆይ ፉማፊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የምዕተ አመቱን የልማት ግቦችን በተለይም በጤናው ዘርፍ ያሉትን ወባ፤ኤች አይ ቪ ኤድስ፤የእናቶችንና ህጻናት ሞት ቅነሳን እያሳካች መሆኗን ተናግረዋል።

ድርጅቱ በወባ ምክንያት ህይወቱን ሊያጣ የነበረ ከ 3 ሚሊዮን በላይ የአፍሪካ ህዝብ ታድጓል።

ያለፈው አመት የድርጅቱ ሊመቀንበር የነበሩት የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ተቋሙ ከእቅዱ 54 በመቶ ያህሉን ማሳካቱን ተናግረዋል።

13 የአፍሪካ አገሮችም በምሰኩ አበረታች ስራዎችን በማከናወናቸው የድርጅቱን ሽልማት ወስደዋል።

ከተሸላሚዎቹ አገሮች መካከል 8ቱ በወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር ስርጭትና በመድሃኒት አቅርቦት አፈጻጸማቸው ባሳዩት እመርታ ነው።

5 አገራትን ደግሞ አጠቃላይ የወባ በሽታን በመከላከል መልካም አፈጻጸም አሳይተዋል።

እኤአ መሰከረም 2009 በታንዛኒያ ዳሬሰላም የተቋቋመው የአፍሪካ መሪዎች ወባ ጥምረት ድርጅት 49 አባል አገራትን ያቀፈ ሲሆን ከምስረታው ጀምሮ እስከ ተያዘው የአውሮፓውያን አመት ድረስ በወባ  ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን ለመታደግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ድርጅቱን በያመቱ እየተቀያየሩ የሚመሩት የአባል አገሮች ጠቅላይ ሚኒስትሮች ወይም ፕሬዝዳንቶች ናቸወ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በቀጣይ አንድ አመት የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን ተመርጠዋል።

– See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/politics/item/1557-2015-02-01-04-31-13#sthash.AManhMTp.dpuf

[Google]