የአንድ ቀን ልጇን በመጥረቢያ የገደለችው በቁጥጥር ሥር ዋለች

0
1063

ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም

በማስረሻ መሐመድ

የአንድ ቀን ዕድሜ ያለትን ሴት ልጇን ‹‹የምተዳደርበትና የማሳድግበት ገቢ የለኝም›› በሚል ሰበብ በአሰቃቂ ሁኔታ በመጥረቢያ ቆራርጣ የገደለችው ተከሳሽ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏን ፖሊስ ገለፀ፡፡ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሴቶችና ሕፃናት ክፍል የወንጀል ምርመራ ኃላፊ ረ/ኢ/ር የሺሀረግ ፈንታሁን እንገለፁልን ተከሳሿ ህዳር 17 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ሲሆን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ የሺ ደበሌ ወረዳ 8 ተብሎ በሚጠራው ሙሉ የተባለችው እና 16 አመት ወጣት የሆነችው ይህቺው ተከሳሽ በዕለቱ የወለደቻትን ሕፃን በመጥረቢያ በመቆራረጥ የቆሻሻ ትቦ ውስጥ በመጣል እሬሳው እንዳይታይም በማለት ውሀ እንደደፋችበት ታውቋል፡፡ ‹‹ጥቆማውን ያደረሰን ተከሳሿ በምትሰራበት ቤት ውስጥ ተከራይታ የምትኖር አንዲት ሴት ደም በማየቷ እና ተከሳሿም እርጉዝ መሆኗን ስለምታውቅ ለቤተሰብ ትነግራለች›› ያሉት ኢ/ር የሻረግ ቤተሰብም ይህንን በማየት ለፖሊስ ወድያውኑ በመጠቆሙ ተከሳሿ  በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንደዋለች አያይዘው ገልፀዋል፡፡  ተከሳሿ በአሁኑ ሰዓት በቁጥጥር ሥር እንደዋለች እና የምርመራ መዝገቡ ተጣርቶ የፍርድ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ረ/ኢ/ር የሻረግ ገልፀዋል፡፡

ረ/ኢ በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት ሕፃናት ላይ የሚፈፀም በደል ህብረተሰቡ በጋራ እንዲከላከል፤ እንዲሁም ወንጀል የሚፈፅሙ አንዳንድ ግለሰቦች ስውር ደበቸው ከፖሊስ ሊያመልጡ እንደማይችሉ በመረዳት ከድርጊቱ ሊታቀቡ ይገባል ብለዋል፡፡

ፖሊስና ርምጃው

[Google]