እህትማማቾቹን ሕፃናት የደፈረው እስራት ተፈረደበት

0
554

ሃይሉ ፍቃዱ 

ፖሊስና ርምጃው

Jan. 31-1-2014

ሁለት እህትማማቾች ሕፃናትን በማታለል ከወሰደ  በኋላ የደፈራቸው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ፍትህ የማሰጠት የስራ ሂደት ሃላፊ ኮማንደር አበበ ተሾመ እንደገለፁት በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ቦንዴ ዳባል ቀ/ገ/ማህበር ልዩ ስሙ ሞጆ ተብሎ የሚጠራው ነዋሪ የሆነው ሻምበል ያዳን ተባለው ላይ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው ነሀሴ 4 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 በሚሆንበት ጊዜ የአጎቱን ሁለት ህፃናት ሴት ልጆችን አፋቸውን
በጨርቅ አፍኖ በመድፈሩ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

እንደ ኮ/ር አበበ ገለፃ ከሆነ ተከሳሹ የህፃናቱ እናት ወደ ገበያ ስትሄድ ልጆቹን እንዲጠብቅ ነግራው እንደሄደች መራቋን አውቆ ሁለት የ6 ዓመት እና የ10 አመት እድሜ ያላቸውን ህፃናት መድፈሩ በሰውና በሀኪም ማስረጃ ከመረጋገጡም በላይ ተከሳሹ ድርጊቱን መፈፀሙን በእምነት ቃሉ አረጋግጧል ብለዋል፡፡ በበቂ ማስረጃ ተጠናክሮ የምርመራ መዝገቡ የቀረበለት በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ታህሳስ 9 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሻምበል ያደን በ18 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

የህፃናቱ ወላጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ ሌሊሴ ኩምሳ በበኩላቸው የአጎቱን ልጆች በደፈረው ተከሳሽ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ቅር እንዳሰኛቸው ተናግረው ልጆቹን የደፈረውን የባለቤቴን ዘመድ በመክሰሴም ከባለቤቴ ጋር በፍቺ ልንለያይ በቅተናል ይላሉ፡፡ ወይዘሮ ሌሊሴ እንደሚሉት ከሆነ የልጆቼ አባት የህፃናት ልጆቹ መደፈር ሳያስቆጨው የዘመዶቼን ስም እያጠፋሽ ስለሆነ ክሱን አቁሚ በማለት ማስጠንቀቂያ ቢሰጠኝም በህግ በኩል ዳኝነቱን ማግኘት በመቻሌ ሊፈታኝ ችሏል ሲሉ ነው የገለፁት፡፡

[Google]