የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት እንደቀጠለ ነው – Press Release

0
2325

Wednesday, 04 December 2013 12:54

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በወያኔው ታጣቂ ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ሲሆን በተሰለፈባቸው አውደ ውጊያዎችም ላይ ከፍተኛ ድል በመቀዳጀት ወታደራዊ የበላይነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡

ለአምባገነናዊ ሥርዓት መንኮታኮት ፍቱን መድሃኒቱ የትጥቅ ትግል መሆኑን የተረዳው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍሎች በተለያዩ ግንባሮች በመንቀሳቀስ ህዝብንና ሀገርን በማሸበርና በማሰቃየት ተግባር ተመድበው ሕብረተሰቡን ቀፍድዶ በመያዝ አንገቱን ቀና አድርጐ እንዳይራመድ በማድረግ ወያኔያዊ ተልዕኮ ያነገቡ የታጠቁ ሃይሎች ላይ ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ የግንባሩ ሠራዊት ኢትዮጵያዊ ኩራት መሆኑን በተጨባጭ እያሳየ ሲሆን በህዳር 24 ቀን 2006 ዓ/ም በታች አርማጭሆ ልዩ ስሙ ዕምባ-ጓዳ በተባለው ቦታ መሽጐ በነበረው የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድን ላይ በሰነዘረው ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ሃያ አንድ (21) የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድኖችን ገድሎ ሃያ ሰባት (27) ያቆሰለ ሲሆን በዚሁ ዕለት በተካሄደው ውጊያ የተለያዩ ከባድና ቀላል መሳሪያዎች ከነመሰል ጥይቶቻቸው ጭምር መማረካቸውንና ከዚሁ ጥቃት ሰለባ ያመለጡት የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድን አባላት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት መቋቋም ተስኗቸው እግሬ አውጪኝ በማለት መሣሪያና ትጥቃቸውን እያዝረከረኩ ለመፈርጠጥ ተገደዋል።

የግንባሩ ሠራዊት በዚህ ቅጥረኛና ምንደኛ ታጣቂ የልዩ ኃይል ላይ በተከታታይ ጊዜ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ የአካባቢውን ሕብረተሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ያስደሰታቸው መሆኑ ሲታወቅ ለዚህ ክቡር ህይወቱን ቤዛ በማድረግ የኢትዮጵያን ህዝብ ከከፋፍለህና ረግጠህ ግዛው ፖሊሲ በማላቀቅ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መመስረት ረሀብና ውሃ ጥም ሳይበግረው እስከ አፍንጫው ከታጠቀው የወያኔ የሚሊሻና የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድኖች ጋር በአፈሙዝ እየተፋለመ ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የሀገር አድን ሠራዊት ጐን በመሰለፍ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።

አንዳንድ የታች አርማጭሆ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ገዢው ቡድን በማን አለብኝነት በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ የጭቆና ቀንበሩን በመጫን በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአርበኞች ግንባርን ትደግፋላችሁና መረጃ ትሰጣላችሁ በማለት የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠረ በበርካታ የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ ላይ አሰቃቂ እርምጃ በመውሰድ ሕብረተሰቡን እንዲሸማቀቅ በማድረግ ተግቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ለዲሞክራሲያው ሥርዓት ግንባታና ለሰብዓዊ መብት መከበር የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል ከመደገፍና ከግንባሩ ጐን በመሰለፍ ሥርዓቱ ሊወገድበት የሚችልበትን መንገድ ከማፋጠንና የትጥቅ ትግሉን ከመደገፍ ሊያግዳቸው የሚችል አንዳችም ኃይል ሊኖር እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡

Source : ኢሕዐግ

[Google]