በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለፀ፣

0
1096
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸውና ድርጅታቸው ዘግተው ከሥራ ውጭ በመሆናቸው። ችግር ላይ ወድቀው እንዳሉ ከከተማዋ ያገኘነው መረጃ አስታወቀ፣
      ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉ ነጋዴዎች መፍትሄ እንዲደረግላቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄያቸዉን ቢያቅርቡም መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ የገለፀው መረጃው። ከአቅማቸው በላይ ግብር መክፈል አቅትዋቸው ድርጅታቸው ከዘጉ ወገኖቻችን ዉስጥ ወ/ሮ የሺወርቅ ዮዉሃንስ ባለ ሆቴል። አቶ ውብ-ኣምላክ ደመላሽ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ነጋዴ የሚገኙባቸው። ሌሎች ያልተጠቀሱ ነጋዴዎች እንዳሉ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣
      በመጨረሻ መረጃው እንደሚያስረዳው። አስቀድመው ግብር ለሚያስከፍሉ የስርዓቱ ተላላኪ ለሆኑ በከተማዋ ውስጥ  ለተመደቡ ሰራተኞች ጉቦ የሚከፍሉና ብጥቅም ለተሳሰርዋቸው በጣት የሚቆጠሩ  ነጋዴዎች ውስን ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል፣
TPDM
[Google]