ፖሊሱን በቡጢ የመታው በቁጥጥር ሥር ዋለ

0
735

Nov. 26, 2o13

በቺካጎ ግዛት ውስጥ አንድ የፀጥታ አስከባሪ ፖሊስን “የለበስከው ዩኒፎርም የቀልድ ነው” በሚል ሰበብ በቡጢ የመታው ተከሣሽ በቁጥጥር ስር ውሎ የፍርድ ውሳኔ እንደተላለፈበት ከወደ አሜሪካ የተሠማው ዜና አመልክቷል፡፡ የ25 ዓመት ዕድሜ ያለው አዲሪው ሎፒዝ የተሰኘው ይኸው ተከሣሽ በእለቱ ጠጥቶ ሲያሽከረክር እንደነበርና በነበረበትም አካባቢ በተነሳው ፀብ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበር የታወቀ ሲሆን ይህንን ሁሉ በቅርብ ርቀት ሲከታተል የነበረውና ቡጢ ያረፈበት ፖሊስ ተከሣሹ ሲያሽከረክር የነበረውን መኪና ከአስቆመ በኋላ መንጃ ፍቃድ ሲጠይቀው ተከሳሹ ከመኪናው በመውረድ “እየቀለድክብኝ ነው አይደል ለሃሎዊን በዓል ብለህ የፖሊስ ዩኒፎርም ለብሰህ እኔ ላይ ታሾፋለህ” በማለት በቡጢ ከመታው በኋላ ፖሊሱ ሲወድቅ በማየቱ ሊያመልጥ በሚዘጋጅበት ወቅት ሌሎች ፖሊሶች መጥተው በቁጥጥር ስር አውለውታል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የቺካጎ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ ላይ የተመሰረቱትን ሦስት ክሶች ከመረመረ በኋላ ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በ7 ዓመት ፅኑ እስራት ሊፈረድበት ችሏል፡፡ ሀሎዊን የተሰኘው የፈረንጆች ባህላዊ ባህል ሲሆን አብዛኛው በአሜሪካኖች ዘንድ የሚከበር ነው፡፡ ባህሉ የተለያዩ አስፈሪ አልባሳትንና ጭንብሎችን በመልበስ አዲስ ዓመትን የሚቀበሉበት ሳምንት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ዘ-ሰን ታይምስ

[Google]