በጎንደር ከተማ የሚገኙ እስር ቤቶች ሃላፊዎች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ነጻ እንለቃችሃለን በሚል ከበርካታ እስረኞች ጉቦ ተቀበሉ፣

0
803

በደረሰን ዘገባ መሰረት የእስር ቤቱ ሃላፊዎች በስራቸው የሚገኙትን እስረኞችን ዓዲሱን ዓመት ምክንያት በማደረግ እንድትለቀቁ የምትፈልጉ ከሆነ በነፍስ ወከፍ 10 ሽህ ብር ክፈሉ የሚል ነገር በዘዴ ውስጥ ውስጡን እንዲነገር ካደረጉ ብሁዋላ አቅሙ ያላቸው እስረኞች የተየጠቁትን ብር ቢከፍሉም እስካሁን ድረስ ግን ከእስር Aልተለቀቁም፣ በዓዲሱ አመተ ነጻ እንወጣለን በሚል ተስፋ ቁጥራቸው 15 የሚደርሱ እስረኞች የተጠየቁትን ገንዘብ በቤተሰቦቻቸው በኩል ከፍለው ሲያበቁ ነጻ ባለመለቀቃቸው ቅር የተሰኙት የእስረኞቹ ቤተሰቦች ጥቅምት
4,2006 ዓ/ም እሚመለከተው ክፍል ድረስ በመሄድ ገንዘባችንን መልሱልን ወይ እስረኞቹን ፍትሉን በማለት ጥያቅያቸውን አቅርበዋል፣ ነገር ግን እናንተ እራሳችሁ ጉቦ በመክፈል እስረኛ ለማስወጣት መሞከራችሁ በህግ ተጠያቂዎች ናችሁ ሲል ሃላፊ ተብየው እዳስፈራራቸው ቷውቋል፣ እንፈታለን በሚል ተስፋ ገንዘብ ከከፈሉ እስረኞች መካከል

-በጋሻው ታፈረ 10 ዓመት የተፈረደበት በግድያ ወንጀል የታሰረ
-አሳምነው መላኩ 12 ዓመት የተፈረደበት በግድያ ወንጀል የታሰረ
-አንጋው ተሞላ 8 ዓመት የተፈረደበትና ወ/ሮ ከበቡ ይገኙበታል::

ትሕዴን

[Google]