በመተማ ወረዳ ማንቲግ በተባለ ልዩ ቦታ የአራት ሰዎች ሬሳ አውላላ ሜዳ ላይ ወድቆ ተገኘ ፣

0
728

20/10/2013

ማንቲግ በተባለ ልዩ ቦታ የአራቱ ሰዎች ሬሳ ወድቆ ከተገኘ ብሁዋላ የአከባቢው መስተዳድር ሁኔታውን ለማጣራት በሚል ምክንያት ጥቅምት 4,2006 ዓ/ም የአከባቢው ኗሪዎችን ሰብስቧል፣ በስብሰባው የተገኙት ኗሪዎች ሰዎቹ የተገደሉት በአከባቢው በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ነው ሲሉ ተደምጠዋል ፣ ሃሳባቸውን በስብሰባው ከገለጹት በአከባቢው ታዋቂ ከሆኑ ሰዎች መካከል አቶ ገ/መድህን ዳኘው ይገኙበታል፣ ቀደም ሲል በዚሁ ወረዳ ሽኸዲ በተባለ ከተማ አንድ የፖሊስ አባል ወደ አከባቢው ስራ ፍለጋ በሄዱ ሁለት ዜጎች ላይ ጥይት ተኩሶ መግደሉን መዘገባችን የሚታወስ ነው::

ትሕዴን

[Google]