ሆዱን ያየ ሆዱን ተወጋ

0
668

ይህ: ግጥም፡ለሆዳቸው: ሲሉ: ህሊናቸውን:በቆራጥነት: ለገበሩ: ወንድምና: እህቶች: መታሰቢያ: ይሁን:: ህዳሴ:ህዳሴ: ብሎ: ለፈለፈ:
ምድረ ሆዳም ሁሉ አሰፈሰፈ
ፍርፋሪ አገኝ ብሎ አነፈነፈ
ከዘረኞች ጋራ ባንዴ ተሰለፈ::
ስማ ሆዳሜ የአገር ሸክም:
ያገኘህ መስሎህ ጥቅማ ጥቅም
አትሯሯጥ አትቀላውጥ
ሀገር ህዝብህን አትሽጥ::
ህዳሴ ህዳሴ ብለው ሲነግሩህ
በደደቢት ቋንቋ ሲያጭበረብሩህ
አንተም አመነሃቸው እውነት መስሎህ
ተከትለህ ስትሮጥ ትንፋሽ እስኪያጥርህ
ትንሽ ባገኝ ብለህ ከሚዘረፈው
የህዝቡን መበደል ክደህ አረፍከው::
ታሪክህ ሲነገር ይኸ ዘመን አልፎ
የክህደትህ መጠን አያልቅም ተጽፎ::
ተው ተመለስ እባክህ ጊዜው ሳይረፍድ ብዙ
ለሆድ ብሎ ማደር ትልቅ ነው መዘዙ
ለትውልድ ይተርፋል ሸክሙና ጓዙ::
ታዛቢ

[Google]