Court Reporting : የእነ እስክንድር ነጋ የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

0
1049
Exclusive to De Birhan from Addis Abeba 
19 Dec 2012


አንዱአለም አራጌ፣ናትናኤል መኮንን እና ክንፈ ገ/ሚካኤል የይግባኝ መከራከሪያ ነጥቦቻቸውን በጠበቃቸው አማካኝነት አቀረቡ፡፡እስክንድር ግን የይግባኝ መከራከሪያ ነጥቦቹን ራሱ ሲያቀርቡ የሚገርም ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡


እስክንድር ላይ የቀረበ የአቃቤ ህግ የክስ ጭብጥ በኢፊድሪ ሕገ-መንግስት መሠረት በአመፅ ያለምርጫ ስልጣን መያዝ ኢ-ሕገመንግስቲዊ ድርጊት ነው፡፡ይህንንም ከግብ ለማድረስ የArab Sprig እንደ ዋቢ አድርገህ ኢትየጵያ ውስጥ እንዲደገም ቀስቅሰሃል፡፡ስለዚህም አሸባሪ ነህ፡፡ የእስክንድር የመከራከሪያ መልሶች 1-የArab Sprig በአንድም የሰሜን አፍሪካ እና የአረብ አገራት የህዝብ እንቅስቃሴ በአመፅ የመንግስት ስልጣንን ለመያዝ የተካሄደ አይደለም፤ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ ለማድረግ እንጂ፡፡በግብፅ፣በቱኒዚያ እና በሊቢያ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ያለምርጫ በህዝባዊ አመፅ ወይም በviolence ስልጣን ላይ የወጣ የለም፡፡


2-የተለያዩ የአለም መንግስታት የኢትዮጵያንም መንግስት ጨምሮ ይህንን የArab Sprig እንቅስቃሴ ለፍትሕ የተደረገ ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ አራት ጊዜ(1987፣1992፣1997 እንዲሁም 2002 ዓ.ም) ምርጫዎች ተካሂደዋል፡፡ነገር ግን አንዱም ነፃ እናፍትሃዊ አልነበሩም፤ይህም ኢ- ገመንግሰታዊ ነው፡፡ስለሆነም በየትኛው የሒሳብ ስሌት ነው የእኔ ይህንን የሕዝብ እንቅስቃሴ በሀገሬ እንዲደገም መፈለግ በሽብርተኝ የሚያስፈርጀኝ?

ሌላው የአቃቢ ህግ የመከራከሪያ ነጥብ የግንቦት ሰባት አባል ነህ የሚል ነበር፡፡ለዚህም የድምፅ እና የፅሁፍ ማስረጃ አቅርቧል፡፡ እስክንድርም ሲመልስ የፅሁፍ ማስረጃውም ግንቦት ሰባት ልሳን ላይ የሚወጡት ፅሁፎች ከእኔ ፅሁፍ ጋር ተመሳሳይነት ስላላቸው ብቻ አባል ነህ ልባል አልችልም፡፡የድምፅ ማስረጃዎቹ ደግሞ ሁሉም በpublicly የተናገርኳቸው ናቸው(በስልክ ተጠለፈ(Interception) የተባለውንም ማስረጃ ይጨምራል)፡፡ታዲያ የት ነው በህብዑ የተንቀሳቀስኩት? አንድም እንኳ በግሌ(Private) ያደርግኩት ግንኝነት እንዴት እንደማስረጃ ማቅረብ ሳይቻል እንዴት ነው በህቡዕ ተንቀሳቅሰሃል የተባልኩት? ሲል ተከራክሯል፡፡

በተጨማሪም አቃቢ ህጉም አንተ ጋዜጠኛ ነህ ፤ ግን ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተገናኘህ የምታደርጋቸው ድርጊቶች ከሙያህ ውጭ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ እንዳለህ ያሳያል በማለት ፍርድ ቤቱን ከዚህ ጋር አያይዞ እንዲያይለት ጠየቀ፡፡እስክንድርም ሲመልስ ከሁሉም ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደርግኩት ንግግርም ሆነ ግንኙነት ሃሳቡ ቀረበው(Initiation) ከራሳቸው ከፓሪቲዎቹ ነበር፡፡ለምሳሌ ከመኢዴፓው ዘመኑ ሞላ ጋር የተደረገው ግንኙነት ሊያካሄዱት ለታሰበው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የእኔ አስተያየት ለምስማት ነበር፡፡(በነገራችን ላይ ስለዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ አስተያየት ከእኔ ብቻ አልነበረም)፡፡ እኔም በዚያ ወቅት የሰጠኃቸው አስተያየት ከቻላችሁት ሰልማዊ ሰልፉን ሰርዙት ፤ካልቻላችሁ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ካለ ማንኛውም አካል የገንዘብም ድጋፍም ሆነ ምንም አይነት ግንኙነት አይኑራችሁ፡፡በተመሳሳይም ኔታ በአንድነት ፓርቲ ላይ ያደረግሁት ንግግር በፓርቲው ተጋብዤ ነበር፡፡

ሌላው የአቃቢ ህግ ክስ ደግሞ እነ እስክንድር የሲቪክ ማህበር በማቋቋም ለሽብር አላማ ማዋል ነበር፡፡የእርሱም ምላሽ የሲቪክ ማህበሩን ልናቋቁም የነበረው ስድስት ሆነን ነበር፡፡ከነርሱም ውስጥ ሁለቱ ተከላካይ ምስክሮች ሆነውኝ ስለማህበሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፤ታዲያ ቀሪ አምስት የማህበሩ አባል በሽብርተኛነት ለምንስ አልተከሰሱም፤ሰዎቹም ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡ታዳያ የፖሊስስ ስራው ምንድን ነው፤እነዚህን አምስት አሸባሪዎች አድኖ ያልያዘው?

በመጨረሻም አንዱአለም አራጌ እኔ ከታሰርኩ ከአንድ አመት ከሶስት ወር ጀምሮ የታሰርኩበት ቦታ የቅጣት ቦታ ወይንም ጨለማ ቤት ነው፡፡ይህ ቦታ እኔ እስከማውቀው ድረስ እዚህ ቦታ የሚታሰር እስረኛ እስር ቤት ውስጥ ባለበት ጊዜ የተለያዩ የዲሲፒሊን ጉድለቶች ያሰየ የሚታሰርበት ነው፡፡እኔ ግን ከታሰርኩ ጀምሮ ከእንደዚህ አይነት ድርጊቶች ንፁህ እንደሆንኩ በግፍ እንድታሰር ተደርጓል፡፡በተጨማሪም ክፍሉ ጠባብ እና አልጋ የሌለው እንዲሁም ወለሉ ትቢያ ነው፡፡የልብ ህመምተኛ በመሆኔ በተለይም ሌሊት የመተንፈስ እያጋጠመኝ ይገኛል፡፡ስለሆነም ክቡር ፍርድ ቤቱ ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ሌላ የመታሰሪያ ክፍል እንድቀየር ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲያሰተላልፍልኝ እጠይቃለሁ፡፡English TranslationThe Federal Supreme Court has heard the appeals of the lawyers of three officials of opposition parties : Andualem Arage, Nathnael Mekonen and Kinfe Gebremichael today. Journalist Eskinder Nega represented himself.  The prosecutor argued that according to the current FDRE Constitution assuming power via protest is unconstitutional, thus the prosecutor said, Eskinder is a ‘terrorist’ and accused him of using ‘the Arab Spring’ as a case and campaigning for it to be repeated in Ethiopia. Eskinder on his part argued that in one of the Northern African countries has the ‘Arab Spring’ been used to unseat regime via violence but the protests were rather held to seek ‘fair and free election’. He said in none of the States such as Libya, Egypt or Tunisia did any political party come to power through violence but election.

Secondly, Eskinder said many countries including the Ethiopian government have hailed the “Arab Spring’ as a protest for “justice”. Four general elections have been conducted in the past 21 years and none of them were free and just which this is unconstitutional. So in what equation does my attempt of for the repetition of this popular movement considered a “terrorist act”, Eskinder argued.

The prosecutor also argued that Eskinder is a member of Ginbot 7 Movement and it presented audio and textual evidences that it said show his membership. Eskinder responded that the mere resemblance of the articles he writes with those that often appear on the Movement’s newspaper doesn’t make him a member of the Movement. Regarding the audio evidences, Eskinder argued that none of the recordings or so called ”interceptions” were not held in private but were conducted in public with media organizations.  

“Therefore in the absence of any evidence that presents any private contact I had with the Movement, how can I be labelled a terrorist?” Eskinder asked. The prosecutor also argued that Eskinder is a journalist but has been in contact with various political parties and this explains that he has his own political agenda. Eskinder said that all the communications and contacts he had were initiated by the parties themselves. 

He said for instance the conversation he had with Zemenu Mola of AllEthiopia Democratic Party (AEDP) was to offer his opinion on the peaceful rally they had planned. “My comment was that they should cancel the protest if possible and if not they should not receive any form of support from Diaspora based organ. Similarly, the speech i made at UDJ party was at the invitation of the party.” Eskinder said. 
The prosecutor also charged Eskinder for publishing a civic organization for “terrorist purposes”.  Eskinder responded saying that they had planned to establish with six other people and while the six other are not caught by the police if the organization was of such nature why only him? 
Finally, the official of the opposition UDJ Party, Andualem Arage said that he was arrested in a dark room for over a year where undisciplined prisoners are kept. The room has no bed and is infested. As I am a cardiac patient, I am frequently having breathing problems during nights, thus I seek the Court to please give an order to the Prison Administration to change him into another cell. The judge stated that he would call the Prison Administration and check Andualem’s case.