16 ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት ከእስር ተፈቱ- መላኩ ተፈራ እና ደበላ ዲንሳ አልተፈቱም

0
910

( ኦክቶበር 5 / 2011 )የቀድሞው የደርግ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት በማረሚያ ቤት የነበራቸውን ባህርይ፣ በወንጀሉ መፀፀታቸው ታይቶና ተገምግሞ የማረሚያ ቤቱ የአመክሮ ቦርድ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ትናንትና ከእስር መፈታታቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ።በአስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት የቡድን መሪ የሆኑት አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ “ከቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ሻለቃ ፍስሃ ደስታ፣ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ፣ ሻምበል ለገሰ አስፋውን ጨምሮ አስራ ስድስት ያህል እሥረኞች ትናንትና ከማረሚያ ቤት ተለቀዋል” ሲሉ አረጋግጠዋል።ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከግንቦት 20 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በ23 የደርግ መንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ፍርድቤት አስተላልፎት የነበረውን የሞት ቅጣት ወደዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት እንዲሻሻልላቸው መወሰናቸውን ተከትሎ ማረሚያ ቤቱ ለፍርድቤት ባቀረበው የአመክሮ ጥያቄ መሠረት በትናትናው ዕለት ከእሥር መለቀቃቸውን የቡድን መሪው አረጋግጠዋል።